Official Announcements From Badr

ኢድ ሙባረክ

Posted by Badr Ethiopia on

ኢድ ሙባረክ

ኢ ድ   ሙ ባ ረ ክ     ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁም በዓለም ለሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለ1441 ኛዉ የኢድ አል ፊጥር (የረመዳን ጾም) በዓል አላህ (ሱ.ወ) በሰላም አደረሰን በማለት በድር ኢትዮጵያ ታላቅ ልባዊ ደስታዉን ይገልጻል።    በዓለማችን የተከሰተዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከመስጂድ እንዲርቅ ቢያስገድደዉም ባለበት ሁሉ ዱዐ (ጸሎት) በማድረግ ፈጣሪዉን ሲማጸን መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በቀጣይ ከዓለማችን በሽታዉ እስኪወገድ ጸሎቱን በበለጠ ልንቀጥልበት የሚገባ አቢይ ጉዳይ ነዉ። አላህ (ሱ.ወ) በሽታዉን ያስወግድልን ዘንድም እንማጸነዋለን።     የዘንድሮዉ በዓል ልዩ የሚያደርገዉ ለሀገራችን እና ለአፍሪካ ኩራት ብሎም ተምሳሌት በሆነዉ በንጉስ ነጃሺ (ፍትሀዊ መሪ) የተሰየመዉ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል በሀገሪቱ ርዕሰ ከተማ ለመገንባት የሚያችል 30000 ካሬ...

Read more →

የስም ለዉጡ እዉን ለምን አስፈለገ ?

Posted by Badr Ethiopia on

የስም ለዉጡ እዉን ለምን አስፈለገ ?

የስም ለዉጡ እዉን ለምን አስፈለገ ?      ለዘመናት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግር ሆኖ ከተጋረጡበት አንዱና ዋነኛዉ ጠንካራ የሆነ ተቋም አለመኖሩ ያስከተላቸዉ ዉስብስብ ችግሮች እንደሆኑ በመገንዘብ  በ 1966 እና በ 2004 የህዝበ ሙስሊሙ ሀገር አቀፍ ተቃዉሞ በጥቁቱ ማሳያዎች ናቸዉ።       በሀገሪቱ በተፈጠረዉ አንጻራዊ ለዉጥ በመንግስትም በኩል ትልቅ ትኩረት ከተሰጣቸዉ ብሎም  መስተካከል እንደሚገባቸዉ ከታመነባቸዉ ተቋማት አንዱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) በመሆኑ አወቃቀሩን አስመልክቶ በአዲስ መልክ ለማደራጀት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ መልካም ፈቃድ ተጀምሮ በተዋቀረዉ የተቋማዊ ለዉጥ ኮሚቴ አማካይነት በቀረበዉ          ጥናታዊ ሰነድ መሰረት ተግባራዊ ለማድረግና ለዉጤት ለማብቃት ደፋ ቀና በሚባልበት በዚህ ወሳኝ ምዕራፍ በማህበረሰቡ መካከል ክፍተቶችን መፍጠር አሳዛኝ...

Read more →

ሀጅ መሀመድ ሰኢድ ወደ አኼራ ሄዱ

Posted by Badr Ethiopia on

ሀጅ መሀመድ ሰኢድ ወደ አኼራ ሄዱ

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁኡን    ሀጅ መሀመድ ሰኢድ ወደ አኼራ ሄዱ ነዋሪነታቸዉ በቶሮንቶ ካናዳ የነበሩት ሀጅ መሀመድ ሰኢድ በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ከትላንት በስቲያ አፕሪል 29 2020 ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ታዉቋል።   ሀጅ መሀመድ ሰኢድ በኢትዮጵያ የፓርላማ አባል በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በ1966 ቱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ንቅናቄም አወንታዊ አስተዋጽኦ ካደረጉ ጠንካራ አባላትም ዉስጥ አንዱ መሆናቸዉና ለመጀሊስ መቋቋምና ዉጤታማነት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ካደረጉት አስተዋጽኦዎች መካከል ጥቂቱ እንደሆነም ይነገርላቸዋል።    ወደ ቶሮንቶ ካናዳ ከመጡም በኋላ በሀገራችን የሙስሊሙን ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ድምጽ ከፍ አድርገዉ በማሰማት ሌት ተቀን ሰለቸኝ ሳይሉ እንዲሁም የቶሮንቶ በረዶ ሳይበግራቸዉ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ታግለዉ ያታገሉ ነበሩ።    ሰዉ ሁሉ ሞትን ይቀምሳታል ነዉና...

Read more →

እንኳን ለ1441ኛዉ የረመዳን ወር አደረሳችሁ

Posted by Badr Ethiopia on

እንኳን ለ1441ኛዉ የረመዳን ወር አደረሳችሁ

  በድር ኢትዮጵያ እንኳን ለ 1441 ኛዉ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን እያለ የዘንድሮዉ ረመዳን በኮረና ቫይረስ (COVID-19) ምክንያት በረመዳን የተለመደዉን የጀምዓ ኢፍጣርና ሰደቃ የሚደረግበት ባለመሆኑ ብዙ ሙስሊም ቤተሰቦችና አካለ ደካሞች በላቀ ችግር ላይ እንደሚሆኑ ግልጽ ነዉ።    ስለሆነም በዚህ የሰደቃና የልግስና ወር የበለጠ ተጠቃሚ እንድንሆን ችግርተኞችን ፤ አቅመ ደካሞችንና ጠዋሪ ያጡትን በየቤታቸዉ እርዳታ እንዲደርሳቸዉ በማድረግ የወርሃ ረመዳን አጅር (ትሩፋት) አፋሽ እንድንሆን ፤ ሁሉም በየአካባቢዉ የእርዳታ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።    እንዲሁም በኮቪድ 19 ምክንያት ችግር ላይ ላሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት በድር ኢትዮጵያ ለሚያደርገዉ ጥረት በጎፈንድሚም ሆነ በየኮምዩኒቲዎቻችን በተዘጋጁ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች በመሳተፍ የድርሻችንን እንድንወጣ እናሳስባለን። ይህንንም ወረርሽን (ኮቪድ19)...

Read more →

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በጋራ እንተባበር

Posted by Badr Ethiopia on

ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በጋራ እንተባበር

  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ በዓለማችን ከፍተኛ ሀብት ፤ ኢኮኖሚ፤ የተደራጀ የህክምና ተቋማት እና በቂ የሰለጠነ የሰዉ ኋይል አላቸዉ የሚባሉ ታላላቅ ሀገራት ሁሉ ሊቋቋሙት ያልቻሉት በፈጣን ወረርሽኝነት   ኮሮና ቫይረስ 19 በመባል የሚታወቀዉ ወረርሽ በርካታ የህዝብ ቁጥር ህይወትን እየቀጠፈ ይገኛል።   ይህ አስከፊ በሽታ በሀገራችን በአሁኑ ወቅት ምንም እንኳን ትንሽ ቁጥር ያለዉ ቢሆንም የማህበረሰባችን የአኗኗር ፤ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ሲታይ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በማሻቀብ በማህበረሰቡም ሆነ በመንግስት ደረጃ ሊቋቋሙት ከሚችሉት በላይ እንደሚሆን ከፍተኛ ግምት እንዳለና ቀደም ሲልም ባወጣነዉ የአቋም መግለጫ ላይ የኛ ድጋፍ ሊቀጥል እንደሚገባ መግለጻችን ይታወቃል። ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ብሎም ከማህበረሰቡ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ከግምት ዉስጥ በማስገባት በድር ኢትዮጵያ ባዋቀረዉ...

Read more →