አስደሳች አበረታች ክንዋኔ

 በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ 

عَنْ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَثَلُ الْمُؤْمِنِينَ فِي تَوَادِّهِمْ وَتَرَاحُمِهِمْ وَتَعَاطُفِهِمْ مَثَلُ الْجَسَدِ إِذَا اشْتَكَى مِنْهُ عُضْوٌ تَدَاعَى لَهُ سَائِرُ الْجَسَدِ بِالسَّهَرِ وَالْحُمَّى

Al-Nu’man ibn Bashir reported: The Messenger of Allah, peace and blessings be upon him, said, “The parable of the believers in their affection, mercy, and compassion for each other is that of a body. When any limb aches, the whole body reacts with sleeplessness and fever.” Ṣaḥīḥ al-Bukhārī &Muslim

  አስደሳች አበረታች ክንዋኔ 

      በዲያስፖራ በምንገኝ ሙስሊም ማህበርረሰብ መካከል ተፈጥረዉ በነበሩ መጠነ ሰፊ ክስተቶች ሳቢያ ልዩነቶች ገነዉ እንደነበር በሁሉም ዘንድ በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ነዉ። በተለይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ የመብት ፤ የህገ መንግስት እና የእምነት ነጻነት መከበር ጥያቄ በሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አማካይነት በይፋ እንቅስቃሴ ከተጀመረ በኋላ በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ኮምዩኒቲዎች መካከል በነበሩ የአካሄድ ልዩነቶች አለመግባባት የተነሳ ትልቅ አሉታዊ የሚባል ተጽዕኖ ማሳደሩም አይዘነጋም ።  በድርን ከመሰረቱ አንጋፋ ኮምዩኒቲዎችም አንዳንዶቹ ሁኔታው መስመር እስከሚይዝ እንዲሁም በኮምዩኒቲ አባላት መካከል ልዩነቶችን ለመቀነስ በሚል ከበድር አባልነታቸዉ ራሳችዉን በጊዜያዊነትም ቢሆን ገትተዉ ቆይተዋል።                                                  

    በወቅቱ የነበሩ ሁኔታዎች እየጠሩ መምጣት ብሎም በሀገራችን እየታየ ያለዉ የለዉጥ ሂደት እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ለቀረቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ የማግኘየት ጅማሮዉ አበረታች መሆኑን ብሎም የሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድነቱን ማጠናከር ግድ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ድርጅቶቻችንን ማጠናከር እንዳለብን በመገንዘብ በካናዳ ካልጋሪ የሚገኘዉ የመዲና ኮምዩኒቲም በወቅቱ ራሳቸዉን አግልለዉ የቆዩ ቢሆንም ቀደም ብለው አባልነታቸዉን በማደስ በድር ኢትዮጵያን ለመቀላቀል ችለዋል። በሲያትል የሚገኘዉ አንጋፋዉ የበድር መስራች የኢማስ ኮምዩኒቲም በድር ኢትዮጵያን የተቀላቀለ እና የ19ኛዉን ኮንቬንሽን ተረክቦ በማዘጋጀት ላይ ያለ ሲሆን በድርን በመስራችነት ከሚታወቁት ሌላኛዉ ከአንጋፋዎቹ አንዱ የሆነዉ ደግሞ በካሊፎርኒያ የሚገኘዉ የሳንሆዜ ETHIOPIAN BAY AREA MUSLIM ASSOCIATION ኮምዩኒቲም ሂደቱን አጠናቀዉ በአላህ (ሱ.ወ) መልካም ፈቃድ በድርን ዳግም ለመጠቀላቀል በቅተዋል።  

     ይህንን አበረታች እንቅስቃሴን ግምት ዉስጥ በማስገባት ሌሎች አንጋፋ የበድር መስራች ኮምዩኒቲዎችም ይሁን አዳዲስ ኮምዩኒቲዎች በድር ኢትዮጵያን እንዲቀላቀሉና ሀይላችንን አጠናክረን የሚጠበቅብንን የድርሻችን እንድንወጣ በማለት በድር ኢትዮጵያ ጥሪዉን በማክበር ያቀርባል።                                            

 አላሁ አክበር !!

በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ  ግንቦት 22 2019

  

 

 

    

Leave a comment

All comments are moderated before being published