The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

በራስ የመተማመናችን ማህተም የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ በዳያስፖራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
እኔም እኮ የኢትዮጵያ ብርሃን ሲበራ፣ ኢትዮጵያ ከድህነት ስትገላገል ተሳትፌያለሁ! አለሁበት! ብለን ለራሳችን ደስታን፣ ለልጅና ለልጅ ልጆቻችን ደግሞ በኩራት የምንናገረው ታሪክ ለማኖር ጭምር በቻልነው እንሳተፍ፡፡
በአሜሪካ የሚገኘው Selam Foundation በዚሁ gofundme ከ10 ሰዓት በፊት ለለገሰው የ$20,000 የአሜሪካን ዶላር ታሪካዊ ስጦታ የከበረ ምስጋና እናቀርባለን! ሌሎች ማህበራትም ይህንን በማየት እየተነሳሱ እንደሆነ እናምናለን!
ስማችን አይጠቀስ (Anonymous) እያላችሁ የለገሳችሁትንም አይተናል! እሱ ይሙላላችሁ! ዳያስፖራው እንዲህ ፍቅር ነው! ለውድ #Ethiopia የማይሆነው የለም!
በአሜሪካን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር አቶ ፍፁም አረጋ

  

   

Newsletter

A short sentence describing what someone will receive by subscribing