Videos
Videos
Official Badr Ethiopia Official Communication
April 12, 2022
Videos
Badr Ethiopia Historical Video Collections
ከበድር ኢትዮጵያ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!!
ለበድር አለም አቀፍ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት አባላት እና ኮሚኒቲዎች፣
በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ዲያስፖራዎች ፣በሀገር ቤት ለምትገኙ ሙስሊሞች እና ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ
አል–አድሀ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት በድር ኢትዮጵያ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!
የኢድ አል አድሀ /አረፋ/ በዓል እኛ የእስልምና እምነት ተከታዮች በነቢዩላ ኢብራሂም ለፈጣሪያቸው ፍፁም ታዛዥነት ፣ ፍቅርና ርህራሄን ያየንበት በልጃቸው ነቢዩላ እስማኤል ደግሞ ፅናትን፣ቁርጠኝነትን እና መስዋዕትነትን
የተማርንበት በመሆኑ በህይወታቸን ታላቅ ቦታ የምንሰጠው እና የነቢያችንን /ሰ.አ.ወ/ ፈለግ በመከተል የምናከብረው በዓል ነው ።
ዘንድሮ እንደሚታወቀው በዓለማችን በተለይ በሙስሊሞች ላይ ብዙ ነገር የደረሰበት
ከመሆኑ ባሻገር መልካም ነገሮችም የታዩበት ነው። በተለይ በሀገራችን ላለፉት 50አመታት በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚፈፀመው በደል
ገደቡን አልፎ ዜጎች በሐገራቸው ሙስሊም በመሆናቸው ማምለክ አይደለም ለመኖር እስኪቸገሩ መፈናፈኛ ያጡበት እና ህገ-መንግስታዊ መብታቸው
ተገፎ እየተሰቃዩ ያሉበት ወቅት ነው።
ዛሬ በየትምህርት ቤቱ ሰላትና ሂጃብ መከልከል ነገ እንደ አክሱም ሌሎች
እስላማዊ የአምልኮ ተግባራትን ወደመከልከሉ ማደጉ አይቀርምና ሁላችንም እንደ አንድ ሆነን በቁርጠኝነት ልንታገለው እንደሚገባ በድር ኢትዮጵያ በዚህ አጋጣሚ ለዚሁ ጉዳይ ባቋቋመው ኮሚቴ ስም ጥሪውን ለማቅረብ ይወዳል።
እስልምናችን በበዓላት ወቅት በጋራ እንድንደሰትና ችግራችንን እንድንካፈል
በሚያዘን መሠረት የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የአክሱም ወገኖቻችንን እያሰብን እንድናከብር በድር ኢትዮጵያ እያስታወስ ይህ የተባረከ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት
የበረከት መልዕክትና ለችግሮቻችንን መፍትሄ ይዞልን የሚመጣ እንዲሆን እየለመንን አላህ (ሱ.ወ) ዒባዳችንን፣ ዱዓችንንና መልካም ሥራችንን እንዲቀበለን፤ በቤታችን፣
በሀገራችንና በዓለም ሁሉ ሰላምና እዝነትን ያስፍን ዘንድ እንማፀነዋለን።
ኢድ
ሙባረክ!
በድር
አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች
May
26, 2026
Blog posts
View all
