ሼህ አብዱልወሀብ ካሳ ወደ አኼራ ሄዱ

Posted by Badr Ethiopia on

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

 ሼህ አብዱልወሀብ ካሳ በትግራይ ክልል በሽሬ የተወለዱ ሲሆን በስደት ከሀገር በመዉጣት በሱዳን፤ በሳኡዲ አረብያ ረጅም ጊዜ ያሳለፉ እና የእስልምና እዉቀት ያካበቱ ሲሆን በመጨረሻም በአሜሪካ ኑሮአቸዉን በማድረግ ላለፉት 42 ዓመታት በትግል እና በኑሮ ከሀገር ዉጭ የኖሩና ረጅሙን የእድሜ ጊዜያቸዉን በሙስሊሙ የትግል እንቅስቃሴ ዉስጥ ያሳለፉ ሲሆን ባደረባቸዉ ህመም በሆስፒታል ሲረዱ ቆይተዉ በትላንትናዉ እለት ወደ አኼራ ሄደዋል። አላህ (ሱወ) ይዘንላቸዉ።

     በሀገራችን የሚፈጸመዉን የሰብአዊ ጥሰትን እና በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰዉን በደልና ሰቆቃ በግልፅ በመቃወም ፤ በመታገል ብሎም በማታገል ይንቀሳቀሱ የነበሩ አክቲቪስት ከመሆናቸዉ አልፎ የብዙዎችን ቀልብ የሳቡ ሰዉ ነበሩ። ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትግል እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና ከመጫወት አንጻር በደፋርነት ወጥቶ ሀሳባቸዉን በመግለጽ መስዋእትነት ከፍሏል።አላህ (ሱብሁዋነሁ ወተአላ) ጄነተል ፊርዶስን ይወፍቃቸዉ ፤ አሜን ።

   ሼህ አብዱልወሀብ ሀገር ቤት ድረስ በመሄድ የቀድሞ የትግራይ ክልላዊ መንግስትን በአክሱም ሙስሊሞች ላይ ያለዉን የግፍ ቀንበር ‘’ማቆሚያ ይበጅለት”” ሲሉ ማንም በመሪዎች ፊት ደፍሮ ያልጠየቀዉን የመብት ጥያቄ በመጠየቅ የሙስሊሙ ህመምና ስቃይ የእርሳቸዉም እንደሆነ በተግባር ያሳዩ ታላቅ ሙጃሂድ ነበሩ።          

     ባጋጠማቸዉ የጤና እክል ምክንያት በተወለዱ በ64 አመታቸዉ ወደ አኼራ በመሄዳቸዉ በድር ኢትዮጵያ በዜና ህልፈት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ፤ በሙስሊሙ ማህበረሰብም ዘንድ ታላቅ ሀዘን ፈጥሯል። አላህ (ሱብሁዋነዉ ወተአላ) የአኼራ ቤታቸዉን እንዲያሳምርላቸዉና ጄነተል ፊርዶስ እንዲወፍቃቸዉ አላህን እንማጸናለን።  ለቤተሰቦቻቸዉ፤ ለትግል ጓዶቻቸውና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በሙሉ መጽናናትን በመመኘት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻላን ።

በድር ኢትዮጵያ      ሰሜን አሜሪካ      አፕሪል 27 2021                    


← Older Post Newer Post →