Official Announcements From Badr

ኢ ድ ሙ ባ ረ ክ

Posted by Badr Ethiopia on

ኢ ድ    ሙ ባ ረ ክ

ኢ ድ    ሙ ባ ረ ክ     በሰሜን አሜሪካ እና በመላዉ ዓለም ለምትገኙ ሙስሊሞች በሙሉ በድር ኢትዮጵያ እንኳን ለ 1440 ኛዉ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል አላህ (ሱ.ወ) በሰላም ፤ በደስታና በፍቅር አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን በደስታ ይገልጻል።    ባለፉት ዓመታት ዋነኛዉ ምኞታችን ዉድ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን እና ከነሱ ጋር ተያያዥነት የነበራቸዉን አካላት በግፍ ለአስከፊዉ እስር በመዳረጋቸዉ ከእስር እንዲፈቱና ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር በሰላም እንዲቀላቀሉ ሁሉም በየፊናዉ የተቻለዉን ሁሉ ጥረት ሲያደርግ  ነበር የቆየዉ።      ለፈጣሪያችን አላህ (ሱ.ወ) የላቀ ምስጋና ይገባዉና ያ ሁሉ አልፎ የህዝበ ሙስሊሙ የረጅም ጊዜ የመጅሊስ ጥያቄም ምላሽ አግኝቶ የእምነት ተቋሞቻችንን ህዝበ ሙስሊሙ በራሱ ለማስተዳደር በሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።...

Read more →

19 ኛዉ የበድር ጉባኤ ተጠናቀቀ­­­­­­­

Posted by Badr Ethiopia on

19 ኛዉ የበድር ጉባኤ ተጠናቀቀ­­­­­­­

  19 ኛዉ የበድር ጉባኤ ተጠናቀቀ­­­­­­­            በድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ላለፉት 18 ዓመታት አመታዊ ጉባኤዉን በሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ስቴቶች ሲያካሄድ ቆይቷል። የዘንድሮዉንም 19ኛዉን ጉባኤ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር በሲያትል ( ኢማስ ) አዘጋጅነት በዋሽንግተን ስቴት በቤልቬዩ ሂልተን ሆቴል ክንዉኑ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል። የኢማስ አባላትም ለፕሮግራሙ መሳካት ያሳዩት የተቀናጀ ሥራ ዉጤት ምስጋናችን የላቀ ሲሆን ለሌሎችም ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል በመተማመን ነዉ፣           በጉባኤዉም በዋነኛነት ትኩረት ተሰጥቶት አንድ መስማሚያ ላይ የተደረሰዉ በድር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ብሎም በሀገራችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ድርጅት እንዲሆን ለማብቃት በጥናት ቡድኑ ተዘጋጅቶ የቀረበዉን ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንዲቻል በቀጣይ ስድስት ወራት ዉስጥ ቅድሚያ ከሚሰጣቸዉ ዋናዎቹ ስራዎች አንዱ...

Read more →

የሀዘን መግለጫ

Posted by Badr Ethiopia on

የሀዘን መግለጫ

                   የሀዘን መግለጫ        አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ዘመናት በተለያዩ ዘርፎች የገጠሟትን ከፍተኛ ፈተናዎች በጽናት ተጋፍጣ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሳለች። ህዝባችን ለተሻለ ለዉጥና ዲሞክራሲ ባደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትግል ሳቢያ በመጣዉ ለዉጥ ወደፊት የመጣዉ የለዉጥ ቡድን በሚሰጠዉ አመራር የሚያኮሩ፤ የሚታዩ ፤ የሚጨበጡ ለዉጦችን በማየት ላይ እና ተዳፍኖ የነበረዉን ዲሞክራሲ በመለማመድ ላይ እንገኛለን።     በዚህ እጅግ አበረታችና ተስፋ ሰጪ የለዉጥ ጎዳና ላይ እያለን ህዝባችንን ያስደነገጠ አገራችንንም በከፍተኛ ፈተና ላይ የጣለ አሳዛኝ ክስተት ቅዳሜ ሰኔ 15/2011 ተፈጽሟል። በዚህ መንግስትን በሃይል የመገልበጥ ሙከራ በተባለዉ አደጋ ምክንያት ሀገራችን ፈተና ላይ ወድቃለች ፤ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችንም አጥታለች ።በድር ኢትዮጵያ ሀገራችን በገጠማት ችግር እንዲሁም ለሞቱ እና ለቆሰሉ...

Read more →

EID MUBARAK

Posted by Badr Ethiopia on

EID  MUBARAK

In the Name of Allah, Most Gracious, Most Merciful                                  Eid Mubarak On behalf of Badr Ethiopia we would like to congratulate you for this special occasion of Eid Al-Fitr and we ask Allah SW to accept our fasting and prayer. Eid as it is described by Prophet Mohamed (Peace and Blessing of Allah be up on him) is an occasion where Muslims have to enjoy and celebrate showing their gratefulness to Allah for all the bounties that He has showered upon us. It is...

Read more →

የመጅሊሱን ህልዉና ማስቀጠል

Posted by Badr Ethiopia on

የመጅሊሱን ህልዉና ማስቀጠል

የመጅሊሱን ህልዉና ማስቀጠል      የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሀገራችን መብቱንና የእምነት ነጻነቱን ለማስከበር ለዘመናት ታግሏል።  በዘመናቱ ዉስጥም በወታደራዊ መንግስት ወቅት የበዓላት እና የሚወከለዉ መጅሊስ ከመመስረት ባሻገር እንደ ዜጋ የመብት መከበር ሊጎናጸፍ አልቻለም። ባለፉት 27 ዓመታትም ይህ ብቸኛዉ ብርቅዬ ድርጅቱን ከህዝበ ሙስሊሙ ለመንጠቅ ብሎም በእምነታችን ዉስጥ ጣልቃ በመግባት ከምንግዜዉም በከፋ ሁኔታ ተጽእኖዉ ቀጥሎ እንደነበር እና በተለያዩ ጊዜያትም ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማዳከም ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል።           የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለዘመናት ሲታገሉለት የነበረዉን የመብት ጥያቄ ከግቡ ለማድረስ በተለይ ባለፉት ሰባት ዓመት እስከ ህይወት መስዋእትነት የተክፈለበት ሰላማዊ የእምነት ነጻነት ጥያቄ ተከናዉኖ አንጻራዊ ምላሽ ማግኘት በጀመረበት በአሁኑ ወቅት ከአባታችን ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ኡመር እድሪስ መጅሊስን በማስመልከት የሰጡትን መግለጫ መላዉ...

Read more →