Official Announcements From Badr

ምስጋና ይገባቸዋል !!!

Posted by Badr Ethiopia on

ምስጋና ይገባቸዋል !!!

ምስጋና ይገባቸዋል !!!      ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዜጎችዋ ደሀዉ ማህበረሰብ በነፍሰ ወከፍ ከተዋጣ ገንዘብ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ስታስገነባ የቆየዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለዉጤት ለማብቃት ደፋ ቀና በሚባልበት በዚህ ፈታኝና ወሳኝ ወቅት በተለይ ከግብጽ በኩል ሰፊ የፖለቲካ ሽፋን ባለዉ መልኩ በህዳሴ ግድቡ ላይ የከፈተችዉ መጠነ ሰፊ የማደናቀፊያ ዘመቻዋ እጅግ መረን በለቀቀ መልኩ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሂደትዋ ወደፊት ይበልጥ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል አለመገንዘብዋ ነዉ።    ዘመቻዉ በተለይ በአረብ አገሮች በአረብኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሽፋን ያለዉ ዘገባ ሌት ተቀን እንደምታካሄድ ከዜና ምንጮች ለመረዳት ይቻላል። ይህንን የግብጾችን ድብቅ አጀንዳም እየተከታተሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በተለያዩ ታዋቂ የዜና ሚዲያዎች እና ሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም በቂ ምላሽ ከመስጠት አልፎ ለማህበረሰባችን...

Read more →

ሼኽ ዶ/ር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ወደ አኼራ ሄዱ

Posted by Badr Ethiopia on

ሼኽ ዶ/ር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ወደ አኼራ ሄዱ

የዘመናችን ታላቁ ዓሊም ሼኽ ዶ/ር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ወደ አኼራ ሄዱ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّـهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ ﴿البقرة እነዚያን መከራ፤በነካቻቸዉ ጊዜ “እኛ ላአላህ ፤ ነን እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን የሚሉትን (አብስር )።        ለሀያ ዓመታት በመካ በኡመል ቁራ ዩኒቨርሲቲ በፕሮፌሰርነት ያገለገሉት ዓለም አቀፍ እዉቅና ያተረፉት ታላቁ ዓሊም ዶክተር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ባደረባቸዉ ህመም በመካ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ በጁን 18 2020 ወደ አኼራ ሄደዋል።      إن الله لا يقبض العلم انتزاعاً ينتزعه من العباد، ولكن يقبض العلم بقبض العلماء، حتى إذا لم يبق عالماً اتخذ الناس رؤوساً جهالاً،...

Read more →

የረጅም ጊዜ የትግል ዉጤት ለድል በቃ

Posted by Badr Ethiopia on

የረጅም ጊዜ የትግል ዉጤት ለድል በቃ

በኢትዮጵያ እምነትን በነጻነት መተግበርና የእምነት ተቋሙም በሀገሪቱ  በአዋጅ ሙሉ እዉቅና እንዲያገኝ ለማስቻል የሙስሊሙ ማህበረሰብ  እጅግ ፈታኝ እና እልህ አስጨራሽ በሆነ መልኩ ከተፈራረቁበት የአጼዎች ነገስታት ጀምሮ በኡለማዎች፤ ምሁራን፤ ወጣቶች፤ ጀመዐዎች ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ቆይቷል። 

   በታሪካዊነቱ የሚዘከርለትና ሁሉን ሙስሊም ማህበረሰብ ባካተተ ሁናቴ ለተቃዉሞ ሰልፍ የበቃዉና ለትግሉ ጅማሮም መሰረት የጣለዉ በ1966 በንጉሱ አጼ ሀይለስላሴ ዘመን ታግለዉ ላታገሉ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።

  

Read more →

ይድረስ ለመጅሊሳችን ከበድር ኢትዮጵያ

Posted by Badr Ethiopia on

ይድረስ ለመጅሊሳችን ከበድር ኢትዮጵያ

ይድረስ ለመጅሊሳችን ከበድር ኢትዮጵያ   የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለመብት ፤ ለእኩልነት፤ ለህገ መንግስት መከበር ያደረጉት እልህ አስጨራሽ መጠነ ሰፊ የትግል እንቅስቃሴ ባደረጉበት ወቅት ሁሉ እንግልት፤ እስር፤ የአካል ጉዳት ፤ ስደት እና የሕይወት መስዋዕትነት መክፈላቸዉ ከታሪክም ሆነ ከቅርብ ጊዜ ትዝታ የምንገነዘበዉ ሀቅ ነዉ። በነዚህ መራር ሂደቶችም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንግቦ ከመነሳት አልታቀበም ።    በሀገራችን በተገኘዉ አንጻራዊ ለዉጥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዘመናት የተጋረጡበትን ችግሮች ደረጃ በደረጃ አቅም በፈቀደ መልኩ መፍትሄ እንዲያገኙ ዘላቂ ትግል ማድረግ ሲገባን በራሳችን በኩል በተፈጠሩ ጥቃቅን የአመለካከት ልዩነቶች ሳቢያ አንድ ሆነን ባለመጓዝ በለዉጡ በአግባቡ ለመጠቀም አልቻልንም።                የመጅሊሱ አወቃቀር ለዉጤት ሲበቃ ከተቋሙ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸዉ ችግሮችም አብረዉ ይቀረፋሉ...

Read more →

አወልያን ለማቋቋም እንዘጋጅ

Posted by Badr Ethiopia on

አወልያን ለማቋቋም እንዘጋጅ

አወልያን ለማቋቋም እንዘጋጅ     በሀገራችን ኢትዮጵያ የሙስሊሙን ማህበረሰብ እገዛና ድጋፍን የሚሹ በርካታ ተግባራቶች ከፊት ለፊታችን ቆመዉ እንደሚጠብቁን ግልጽ ነዉ። ለዚህም ዋነኛዉ ምክንያት ለዘመናት ሙስሊሙን ማህበረሰብ አንቀሳቅሶ በየጊዜያቱ ሰብዓዊ መብቶችንና መሰል ሂደቶችን የሚያስፈጽም ሁነኛ አካል አለመኖሩም ነበር።     በአወልያ በ2004 የተቀጣጠለዉ ህዝባዊ አመጽ ሀገራዊ ለዉጡን አስከትሎ ለድል ሲበቃ ሌሎችንም በርካታ መሰረታዊ ለዉጦችንም አያያዞ አስመዝግቧል። የትግሉ ፈር ቀዳጅ ፤ የአሻራችን ጥንስስ የተጣለበት አወልያ አሁን ደግሞ የእኛን ድጋፍ ይፈልጋል። የዚሁ ባለዉለታ ተቋማችን ያለበትን አደረጃጀት ለማሻሻል ብሎም ዘላቂነት ባለዉ መልኩ ለማቋቋም እንዲቻል በሀገር ቤት እና ከሀገር ቤት ዉጭ ግብረ ሃይል ተዋቅሮ በቅድሚያ ለትዉልድ ታሪክና ዘመን ተሻጋሪ በሆነዉ ስራ ’’ ሆስፒታሉን እናስጨርስ’’ በሚል መርህ የገንዘብ...

Read more →