Official Announcements From Badr

መፍትሄ ያጣዉ የንጹሀን ዜጎች እልቂት

Posted by Badr Ethiopia on

መፍትሄ ያጣዉ የንጹሀን ዜጎች እልቂት

መፍትሄ ያጣዉ የንጹሀን ዜጎች እልቂት     በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የንጹሀን ዜጎች ህይወት ያለምንም ሰብአዊ ርህራሄ ዘግናኝ በሆነ መልኩ ሲቀጠፍ መስማት፤ ማየት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ መገንዘብ አቅቶን ነዉ ወይንስ አለመታደል ብለን እንለፈው? ሁሉም አካላት በራሳችዉ መሰል ድርጊቶችን ቢያወግዙም ሊታቀብ ያልቻለ ዘግናኝ ኢሰብአዊ ጥፋት በንጹሀን ዜጎች ላይ ቀጥሏል ።    ንጹሀን ዜጎች በሀገራቸዉ ያለምንም ከልካይ በነጻነት መንቀሳቀስ ሲገባቸዉ ለመሸማቀቅ፤ ለመጨነቅ መዳረጋቸዉ ብሎም ፍትህን እየናፈቁ መንከራተትን ሁሉም ዜጋ ትኩረት ሰጥቶ ቆም ብሎ በማሰብ ከምንም ነገር በፊት ቅድሚያ በመስጠት ሊያስብበት የሚገባ ዋነኛዉ መፍትሄ የሚሻ ሀገራዊ ጉዳይ ነዉ።    በምዕራብ ወለጋ በጉሊሶ ወረዳ የተካሄደዉ የንጹሀን ዜጎች ጅምላ ጭፍጨፋ መልስ ያጣ ዘግናኝ ድርጊት በምን...

Read more →

ለፈረንሳዩ መሪ የተሰጠ የተቃዉሞ ምላሽ

Posted by Badr Ethiopia on

ለፈረንሳዩ መሪ የተሰጠ የተቃዉሞ ምላሽ

ኡለፈረንሳዩ መሪ የተሰጠ የተቃዉሞ ምላሽ       የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት አማኑኤል የሀሳብ ነጻነትን ሽፋን በማድረግ በነቢዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰላም ) ላይ የሰነዘሩትን ከአንድ መሪ የማይጠበቅ ጸያፍ ንግግርን በድር ኢትዮጵያ በጽኑ ያወግዛል ። በዓለም አንድ ሶስተኛ በሚሆነዉ ሙስሊም ልብ ዉስጥ የነገሱትን ተወዳጁ ነብይ (ሰዐወ) በአደባባይ እየወጡ ማላገጥና የሰብዕናቸዉን ልዕልና ለማዉረድ መሞከር ስለእምነት እዉቀቱ የሌላቸዉ መሆኑን የሚጠቁም ሲሆን በሌላ መልኩ የሀሳብ ነጻነት ምንም አይነት ህጋዊ ክልከላ የማይካሄድበት ከሆነ ደግሞ ስለሌሎች ዲሞክራሲያዊ መብት በእኩል አለመገንዘብ ሌላዉ ችግር ነዉ ። የሀሳብ ነጻነት በቁጥር ትንሽነት ወይንም ብዛት የማይለካ ከመሆኑ አንጻር በአዉሮፓ ዉስጥ ለሚገኙ ሙስሊሞች ግዴለሽነትን ከማሳየቱ አልፎ ለማሸማቀቅና የእስልምና ጥላቻ (Islamophobia) በግልጽ ያሳያል።   ፈረንሳይ በቅኝ...

Read more →

በጉራፈርዳ የንጹሀን ዜጎች አሰቃቂ ግድያ

Posted by Badr Ethiopia on

በጉራፈርዳ የንጹሀን ዜጎች አሰቃቂ ግድያ

በጉራፈርዳ የንጹሀን ዜጎች አሰቃቂ ግድያ    በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ በንጹሀን ላይ የተፈጸመዉ ግድያዎች እጅግ አሳዝኖናል። የሀገራችን የሰላም ጉዳይ ከእለት ወደ እለት ይሻሻላል የሚል ተስፋ ብንሰንቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመምጣቱ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ በመድረሱ የሀገሪቱን ሰላም እየሽረሸረ ይገኛል።    የንጹሀን ግድያና መፈናቀል በጣም ከመዘዉተሩ የተነሳ ሰምተንም ቢሆን  የማያስደነግጠንና የተለመደ እየሆነ የመምጣቱ ሂደቱ የምንጓዝበትን የለዉጥ መንገድ እንዳያሰናክልብንና የምናልማትን የበለጸገች ኢትዮጵያን የማየት ምኞታችንን እንዳያጨልምብን ቀድመን ነቅተን እንደ ዜጋም እንደ መንግስትም ልንከላከል የሚገባ ሲሆን በትክክል ችግራችንን ለይተን በጋራ በመቆም መፍትሄ ለመፈለግ ቁርጠኛ አቋም መዉሰድ ያለብን ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሰናል።    የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ሀላፊነት ትልቁ ድርሻ የመንግስት በመሆኑ መንግስትም...

Read more →

የበድር ቦርድ ምርጫ ማካሄዱን ስለማሳወቅ

Posted by Badr Ethiopia on

የበድር ቦርድ ምርጫ ማካሄዱን ስለማሳወቅ

የበድር ቦርድ ምርጫ መካሄዱን ሰለማሳወቅ     የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በቦርድ የሚመራ ድርጅት ሲሆን ባለፉት ዓመታት በድርጅቱ ተከስተዉ በነበሩ ዉስጣዊና ዉጫዊ ችግሮች ሳቢያ ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ ያልተካሄደ ቢሆንም በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ምርጫዎችም ቢሆን በተወሰኑ አካላት የተደረገ ሽግሽግ እንደነበር ይታወቃል።    ሆኖም በ20ኛዉ የበድር ጉባኤ ወቅት ይደረጋል ተብሎ በእቅድ የተያዘዉ የቦርድ እና የስራ አስኪያጆች ምርጫ     በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አማካይነት ጉባኤዉ አለመካሄዱ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት እንደ ባህልም ሆኖ በድርጅቱ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ምርጫ መደረጉ ቀደም ሲል በነበረዉ ተለምዶ እየተከናወነ ቢዘልቅም ዘንድሮ ጉባኤዉ ባለመካሄዱ ምርጫዉም ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።      በአሁኑ ወቅት የኮምዩኒቲዎችም ሆነ የቦርድ አባላት ቁጥር ቀደም...

Read more →

መልካም ተግባር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል

Posted by Badr Ethiopia on

መልካም ተግባር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል

መልካም ተግባር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል    በሀገራችን ለረጅም ዘመናት መልስ ካጡ ጉዳዮች በከፊል ለዉጤት እየበቁ ወይንም ምላሽ እያገኙ መሄዳቸዉ አበረታች ተግባር በመሆናቸዉ ሊበረታቱ ይገባል እንላለን። በተለይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሰረታዊ ጥያቄ ሆነዉ አስተዋሽ ተነፍጎአቸዉ ሲንከባለሉ የነበሩት ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች ዋነኛዎቹ ናቸዉ።    በ2007 እኤአ የበድር ልዑካን ቡድን በበርካታ ጉዳዮች ጥናታዊ ጽሁፍ አዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ከፍተኛ አካላት ሲያቀርብ የፋይናንስ ተቋማትን በተመለከተ  “ ከሙስሊም ባህል አኳያ የተቀረጹ የፋይናንስ ተቋማትም አስፈላጊ በመሆናቸዉ ማደራጀት እና ከወለድ ነጻ የሆኑ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት ቢቋቋሙ ከሁሉም በላይ ወለድ ዉስጥ ላለመግባት ከኢንቨስትመንት የታቀቡ ዜሆችን በልማት ለማሳተፍ አይነተኛ ሚና ይኖራቸዋል ፤ ድህነትን ለመቀነስ የሚደረገዉ...

Read more →