ግድቡ የኔ ነዉ      It Is My Dam

                      ግድቡ የኔ ነዉ      It Is My Dam

የመሰረተ ልማትና አገልግሎቶች አቅርቦት እጦት ሰፊዉን የሀገራችን ህዝብ ለከፋ ችግር በመዳረግ የመከራ ጊዜ እንዲገፋ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሀገራችን ሰዉ ሰራሽና ተፈጥሮ ያደላትን ጸጋ አሟጣ መጠቀም አማራጭ የሌለዉ መፍትሄ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለሀገራችን ኢትዮጵያ ልማት ትልቅ ዋልታና የአንድነት ተምሳሌት እንደሚሆን ተስፋ የተጣለበት የህዳሴ ግድቡ ግንባታ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ሕዝባችንም በቅርቡ የሚደረገዉን የግድቡን ሁለተኛ ዙር የዉሀ ሙሌት ከግንባታ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚሸጋገርበት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆኑን በማመን በአንክሮ እየጠበቀ ይገኛል። ይህ ታላቅ አገራዊ ፕሮጀክት በታቀደለት  መርሀ ግብር መሰረት በቶሎ እንዲጠናቀቅ የሁላችንም ተሳትፎና ርብርብ እጅግ በጣም ያስፈልጋል። በዚህ ፕሮጀክት ላይ የምናደርገዉ ተሳትፎ “ ግድቡ የኔ ነዉ! “ ብሎ አደባባይ የወጣዉን ወገናችንን “አለሁልህ ለልማትህ ከጎንህ ነን” እንደማለትና ይህንንም በተግባር የሚያሳይ ፤ ህያዉና ዘመን የሚያሻግር ሀዉልት እንደማቆም የሚቆጠር ነዉ።   

በድር ኢትዮጵያ የግድቡ ሀገራዊ ፋይዳና ግንባታዉ የደረሰበትን ወሳኝ ምዕራፍ በማሰብ የግንባታዉን ሥራ የሚደግፍ ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ቡድን (ታስክ ፎርስ) በማቋቋም ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ሥራ ገብቷል። ቡድኑ በዲያስፖራ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን የድርሻቸዉን ለማበርከት እድል የሚፈጥርና ሁሉንም በጋራ ተሳታፊ የሚያደርግ እንደመሆኑ መጠን በጁን 26, 2021 በተዘጋጀዉ በዙም የገንዘብ አሰባሰብ መርሀግብር ላይ በመገኘት የበኩላችሁን ድርሻ እንድታበረክቱ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን ።     

Zoom Meeting Link                                 https://us02web.zoom.us/j/89275003161pwd=cHE4a3h0d3JIMmJjTWlIVHlhUm55QT09

ጁን 26, 2021     ሰዓት 2 pm Eastern  

          Meeting ID: 831 5910 4022        pass code 317759                                                                                              በድር ኢትዮጵያ       ሰሜን አሜሪካ      ጁን 20, 2021

 

Leave a comment

All comments are moderated before being published