ለፈረንሳዩ መሪ የተሰጠ የተቃዉሞ ምላሽ

ኡለፈረንሳዩ መሪ የተሰጠ የተቃዉሞ ምላሽ  

    የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት አማኑኤል የሀሳብ ነጻነትን ሽፋን በማድረግ በነቢዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰላም ) ላይ የሰነዘሩትን ከአንድ መሪ የማይጠበቅ ጸያፍ ንግግርን በድር ኢትዮጵያ በጽኑ ያወግዛል ። በዓለም አንድ ሶስተኛ በሚሆነዉ ሙስሊም ልብ ዉስጥ የነገሱትን ተወዳጁ ነብይ (ሰዐወ) በአደባባይ እየወጡ ማላገጥና የሰብዕናቸዉን ልዕልና ለማዉረድ መሞከር ስለእምነት እዉቀቱ የሌላቸዉ መሆኑን የሚጠቁም ሲሆን በሌላ መልኩ የሀሳብ ነጻነት ምንም አይነት ህጋዊ ክልከላ የማይካሄድበት ከሆነ ደግሞ ስለሌሎች ዲሞክራሲያዊ መብት በእኩል አለመገንዘብ ሌላዉ ችግር ነዉ ። የሀሳብ ነጻነት በቁጥር ትንሽነት ወይንም ብዛት የማይለካ ከመሆኑ አንጻር በአዉሮፓ ዉስጥ ለሚገኙ ሙስሊሞች ግዴለሽነትን ከማሳየቱ አልፎ ለማሸማቀቅና የእስልምና ጥላቻ (Islamophobia) በግልጽ ያሳያል። 

 ፈረንሳይ በቅኝ ግዛት የአፍሪካን ህዝብ በቀን ሰራተኛነት ወደ ሀገሯ ያስገባችና ለብዙሀኑ ንጹሀን ዜጎች ሞትና እንግልት ተጠያቂ የሆነችዉ ዛሬ ላይ ስለ ሀሳብ ነጻነት የማስተማር ሞራልም ብቃትም የላትም ። ዛሬም ድረስ ለህዝቦቿ እኩልነትን ያላረጋገጠችዉ ለፈረንሳይ ዜጎች የምንገልጸዉ በሌሎች እምነት ላይ ጣልቃ ከመግባት ይልቅ በቅድሚያ የሀሳብ ነጻነትን መሪያቸዉን  ለመቃወምና ስልጣናቸዉን ያለአግባብ የሚጠቀሙትን ወጥቶ ለማናገር እንዲያዉሉት እንመክራቸዋለን።

   ለፈረንሳዩ መሪ ማክሮን ፤ የሰዉ ልጅ ይመጣል ይሄዳል አንተም ይህችን ምድር ለቀህ ትሄዳለህ ፤ የአንድ ህዝብ ስልጣኔም አንዴ ከፍ ሲል ሌላ ጊዜ ዝቅ ብሎ ይወድቃል ፤ ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ያለብህ ረሱል (ሰዐወ) ትተዉልን የሄዱት መንገድና ሙስሊሙ ለሳቸዉ ያለዉ ፍቅር አንተና ሀገርህ የወረደ ታሪካችሁ በመጽሀፍ ከተጻፈ ደግሞ ለረዥም ዘመናት ይሮራል። በቁራዐንም እንደገለጻቸዉ  “ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍۢ “  “አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ “ ( አልቀለም ፤ 4 ) ነብዩ ሙሀመድ ለሰዉ ዘር ሁሉ በእዝነት የተላኩ ነብይ መሆናቸዉን በተግባርም ኑረዉት እንዳሳዩን ቁርዐንም ምስክር ነዉ። እናም የሳቸዉን ስብዕና ዝቅ ለማድረግ የሚሞክር ሁሉ እሱ ዝቅ ያለና እራሱን ያዋረደ ብቻ ነዉ።

ፊዳክ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ (ሰ ዐ ወ )                                                                             ፊዳክ ሩሂ ወደሚ ያሀቢበሏህ (ሰ ዐ ወ )       

አላሁ አክበር                  

              በድር ኢትዮጵያ     ሰሜን አሜሪካ    ኦክቶበር 30 2020­­­                                     

Leave a comment

All comments are moderated before being published