የበድር ቦርድ ምርጫ ማካሄዱን ስለማሳወቅ

የበድር ቦርድ ምርጫ መካሄዱን ሰለማሳወቅ

    የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በቦርድ የሚመራ ድርጅት ሲሆን ባለፉት ዓመታት በድርጅቱ ተከስተዉ በነበሩ ዉስጣዊና ዉጫዊ ችግሮች ሳቢያ ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ ያልተካሄደ ቢሆንም በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ምርጫዎችም ቢሆን በተወሰኑ አካላት የተደረገ ሽግሽግ እንደነበር ይታወቃል።

   ሆኖም በ20ኛዉ የበድር ጉባኤ ወቅት ይደረጋል ተብሎ በእቅድ የተያዘዉ የቦርድ እና የስራ አስኪያጆች ምርጫ     በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አማካይነት ጉባኤዉ አለመካሄዱ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት እንደ ባህልም ሆኖ በድርጅቱ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ምርጫ መደረጉ ቀደም ሲል በነበረዉ ተለምዶ እየተከናወነ ቢዘልቅም ዘንድሮ ጉባኤዉ ባለመካሄዱ ምርጫዉም ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።

     በአሁኑ ወቅት የኮምዩኒቲዎችም ሆነ የቦርድ አባላት ቁጥር ቀደም ሲል ከነበረዉ በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ጉባኤዉን መጠበቅ የግድ ባለመሆኑና የድርጅቱንም አቅም ባለዉ የሰዉ ሀይል ለመገንባት እንዲያስችል በሚል በታቀደዉ መሰረት የበድር ቦርድ አባላት ምርጫ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ መሰረት የድርጅቱ

  1. ሊቀመንበር ወንድም አህመድ ወርቁ ከሰላም ፋውንዴሽን ኮምዩኒቲ ፤ ቨርጂኒያ
  2. ምክትል ሊቀመንበር ወንድም አህመድ መሀመድ ከነጋሺ ኮምዩኒቲ ፤ ቶሮንቶ ካናዳ
  3. ዋና ጸሀፊ ወንድም ኢብራሂም ኢማም ከኢማስ ኮምዩኒቲ ፤ ሲያትል ሆነዉ ተመርጠዋል።

   ከዚህ ቀደም ለረጅም ጊዜ ደከመኝ ፤ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነትና በትጋት ድርጅቱን ሲያገለግሉ የቆዩት ወንድም አብዱልቃድር አህመድ ሊቀመንበር ከቶሮንቶ ካናዳ ፤ ዶ/ር አብዲ ያሲን ምክትል ሊቀመንበር ከዳላስ ቴክሳስ ፤ ወንድም ሳላሀዲን አብዶ ምክትል ሊቀመንበር ከዊኒፔግ ካናዳ  ፤  ወንድም አብዱልሀዲ ዴብሳ ዋና ጸሀፊ ከሲያትል በመሆን ያገለገሉ እና ጊዜያቸዉን ፤ እዉቀታቸዉን ብሎም ገንዘባቸዉን መስዋዕት በማድረግ ለድርጅቱ እና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ላደረጉት ጥረት በድር ኢትዮጵያ የላቀ ምስጋና ያቀርባል።   

      በአሁኑ ወቅት የመተካካቱ ሰራ በሰላማዊ መንገድ የተጠናቀቀ ሲሆን በአዲስ መልክ የተዋቀረዉ የቦርድ አካላትም  በቀጣይ የስራ አስኪያጅ አመራር አባላትን የማዋቀር ሂደት የሚጀመር መሆኑን እያሳወቅን ቀጣይ ሂደቱንም እንደ ደረጃዉ ወደፊት የምናሳዉቅ መሆናችንን እንገልጻለን።

    አላሁ አክበር

              በድር ኢትዮጵያ     ሰሜን አሜሪካ    ኦክቶበር 21 2020­­­                                                                                                           

Leave a comment

All comments are moderated before being published