በአርሲ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት እናወግዛለን !!

CONDEMNATIONBadr Ethiopia

በአርሲ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት እናወግዛለን !! 

በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት  "በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሴኮ፣ በሸርካ፣ በሙግቶ፣ በበሌ እና በመንዲዳ ወረዳዎች  የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው" ይህ ጥቃት ለዘመናት አብሮ በመኖር እሴት በምትታወቀው አገር ላይ የተፈጸመ ታላቅ በደል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቆም ዘንድ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግና ወንጀለኞቹ በአሰቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ እንዲያደርግ በድር ኢትዮጵያ ጥያቄውን ያቀርባል። 

ትናንትና የተወሰኑ ፅንፈኛ ቡድኖች በሞጣና በጎንደር ሙሰሊሞች ላይ የፈፀሙት አሰነዋሪና ዘግናኝ ጥቃት እንዳመመን ሁሉ ዛሬ በተደጋጋሚ በአርሲ ንፁሀን ላይ የተፈፀመው ጥቃት ነገም እንዳይቀጥል ሁላችንም  እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነት መቆም ይኖርብናል። 

በመሆኑም  ለመንግስት እና ለየጸጥታ አካላት ባስተላለፉት ይህ ግድያ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና የየደረጃው ኃላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ ድር ኢትዮጵያ በጥብቅ ያስገነዝባል። 

በድር አለም ዐቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት 

June 5, 2026, Washington, DC 

የሐዘን መግለጫ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

የሐዘን መግለጫ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

CONDOLENCESBadr Ethiopia

بسم الله الرحمن الرحيم

የሐዘን መግለጫ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ ﴿١٥٦﴾

እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡ (156)

በድር ኢትዮጵያ የቀድሞው የአዲሰ አበባ ከንቲባ የነበሩት አምባሣደር አሊ አብዶ ወደ አሄራ መሄድ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል።

 የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አምባሳደር ዓሊ አብዶ  በሕየወት ዘመናቸው ለሀገራቸው እንደዜጋ ለእምነታቸው እንደ ሞዕሚን ለፈፀሟቸው አበርክቶዎች በድር ኢትዮጵያ እውቅና ይሰጣል

አምባሳደር አሊ አብዶ በተለይም 27ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበሩባቸው ከ1990 - 1995 አምስት አመታት ሙስሊም ጠል በሆኑ የቢሮክራሲው ቡድን አባላት  በመሰጂዶች አካባቢ የሚፈፅመውን ደባ በመበጣጠስ ፍትሐዊ የአምልኮ ሥርዐት እንዲኖር ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚታወሱ ናቸው።

አምባሳደር ዓሊ አብዶ በአርሲ ዴራ ከተማ ከአባታቸው አቶ ዓሊ ሱለይማንና ከእናታቸው ወ/ሮ አፀደ ወልደማሪያም የተወለዱ ሲሆን ከትዳር አጋራቸውም ሶስት ሴቶች እና አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል።

አምባሳደር ዓሊ አብዶ በስራ ዘመናቸው ሁሉ ሐገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት፣ በታማኝነትና በታታሪነት ሲያገለግሉ ነበር። በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት  አላህ ለአምባሳደር ዓሊ አብዶን  ጀነተል ፊርደውስ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ላገለገሉት ሕዝብ ደግሞ መፅናናትን እንዲሰጥ ይማፀናል።

በድር አለም ዐቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት

June 5, 2026, Washington, DC

United Through Our Member Communities

First Hijrah Foundation || Selam Foundation || Negashi Atlanta ||  Bilal Dallas   ||   Al-Amin Houston ||   EYMAN Nashville  || EMAS Seattle  ||  DarulIman Sun Diego  || Nejashi Toronto  ||   Abyssinia Winnipeg  || Medina United Calgary  ||  Nejashi New Zealand  || EBAMA Sun Jose || Lugman Boston  || Bilal Ethiopians Alberta ||  More ...

EID MUBARAK

PRESS RELEASEBadr Ethiopia

بسم الله الرحمن الرحيم

ከበድር ኢትዮጵያ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!!

ለበድር አለም አቀፍ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት አባላት እና ኮሚኒቲዎች፣ በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ዲያስፖራዎች ፣በሀገር ቤት ለምትገኙ  ሙስሊሞች እና ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል–አድሀ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት በድር ኢትዮጵያ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!

የኢድ አል አድሀ /አረፋ/ በዓል  እኛ የእስልምና እምነት ተከታዮች  በነቢዩላ ኢብራሂም ለፈጣሪያቸው ፍፁም ታዛዥነት ፣ ፍቅርና ርህራሄን ያየንበት  በልጃቸው ነቢዩላ እስማኤል ደግሞ ፅናትን፣ቁርጠኝነትን እና መስዋዕትነትን የተማርንበት በመሆኑ በህይወታቸን ታላቅ ቦታ የምንሰጠው እና የነቢያችንን /ሰ.አ.ወ/  ፈለግ በመከተል የምናከብረው በዓል ነው ።

ዘንድሮ እንደሚታወቀው በዓለማችን በተለይ በሙስሊሞች ላይ ብዙ ነገር የደረሰበት ከመሆኑ ባሻገር መልካም ነገሮችም የታዩበት ነው። በተለይ በሀገራችን ላለፉት 50አመታት በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚፈፀመው በደል ገደቡን አልፎ ዜጎች በሐገራቸው ሙስሊም በመሆናቸው ማምለክ አይደለም ለመኖር እስኪቸገሩ መፈናፈኛ ያጡበት እና ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተገፎ እየተሰቃዩ ያሉበት ወቅት ነው።

ዛሬ በየትምህርት ቤቱ ሰላትና ሂጃብ መከልከል ነገ እንደ አክሱም ሌሎች እስላማዊ የአምልኮ ተግባራትን ወደመከልከሉ ማደጉ አይቀርምና ሁላችንም እንደ አንድ  ሆነን በቁርጠኝነት ልንታገለው እንደሚገባ በድር ኢትዮጵያ  በዚህ አጋጣሚ ለዚሁ ጉዳይ ባቋቋመው ኮሚቴ ስም ጥሪውን ለማቅረብ ይወዳል።

እስልምናችን በበዓላት ወቅት በጋራ እንድንደሰትና ችግራችንን እንድንካፈል በሚያዘን መሠረት የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የአክሱም ወገኖቻችንን እያሰብን እንድናከብር  በድር ኢትዮጵያ እያስታወስ ይህ የተባረከ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት የበረከት መልዕክትና ለችግሮቻችንን መፍትሄ ይዞልን የሚመጣ እንዲሆን እየለመንን  አላህ (ሱ.ወ) ዒባዳችንን፣ ዱዓችንንና መልካም ሥራችንን እንዲቀበለን፤ በቤታችን፣ በሀገራችንና በዓለም ሁሉ ሰላምና እዝነትን ያስፍን ዘንድ እንማፀነዋለን።

ኢድ ሙባረክ!

በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች

May 26, 2026