የሐዘን መግለጫ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

የሐዘን መግለጫ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

CONDOLENCESBadr Ethiopia

بسم الله الرحمن الرحيم

 

የሐዘን መግለጫ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

 

الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ ﴿١٥٦﴾

እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡ (156)

 

በድር ኢትዮጵያ የቀድሞው የአዲሰ አበባ ከንቲባ የነበሩት አምባሣደር አሊ አብዶ ወደ አሄራ መሄድ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልፃል።

 የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አምባሳደር ዓሊ አብዶ  በሕየወት ዘመናቸው ለሀገራቸው እንደዜጋ ለእምነታቸው እንደ ሞዕሚን ለፈፀሟቸው አበርክቶዎች በድር ኢትዮጵያ እውቅና ይሰጣል

አምባሳደር አሊ አብዶ በተለይም 27ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበሩባቸው ከ1990 - 1995 አምስት አመታት ሙስሊም ጠል በሆኑ የቢሮክራሲው ቡድን አባላት  በመሰጂዶች አካባቢ የሚፈፅመውን ደባ በመበጣጠስ ፍትሐዊ የአምልኮ ሥርዐት እንዲኖር ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚታወሱ ናቸው።

አምባሳደር ዓሊ አብዶ በአርሲ ዴራ ከተማ ከአባታቸው አቶ ዓሊ ሱለይማንና ከእናታቸው ወ/ሮ አፀደ ወልደማሪያም የተወለዱ ሲሆን ከትዳር አጋራቸውም ሶስት ሴቶች እና አንድ ወንድ ልጅ አፍርተዋል።

አምባሳደር ዓሊ አብዶ በስራ ዘመናቸው ሁሉ ሐገራቸውንና ሕዝባቸውን በቅንነት፣ በታማኝነትና በታታሪነት ሲያገለግሉ ነበር። በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት  አላህ ለአምባሳደር ዓሊ አብዶን  ጀነተል ፊርደውስ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ላገለገሉት ሕዝብ ደግሞ መፅናናትን እንዲሰጥ ይማፀናል።

በድር አለም ዐቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት

June 5, 2026, Washington, DC

United Through Our Member Communities

First Hijrah Foundation || Selam Foundation || Negashi Atlanta ||  Bilal Dallas   ||   Al-Amin Houston ||   EYMAN Nashville  || EMAS Seattle  ||  DarulIman Sun Diego  || Nejashi Toronto  ||   Abyssinia Winnipeg  || Medina United Calgary  ||  Nejashi New Zealand  || EBAMA Sun Jose || Lugman Boston  || Bilal Ethiopians Alberta ||  More ...