በአርሲ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት እናወግዛለን !!

በአርሲ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት እናወግዛለን !!

CONDEMNATIONBadr Ethiopia

በአርሲ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት እናወግዛለን !! 

በድር አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት  "በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሴኮ፣ በሸርካ፣ በሙግቶ፣ በበሌ እና በመንዲዳ ወረዳዎች  የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው" ይህ ጥቃት ለዘመናት አብሮ በመኖር እሴት በምትታወቀው አገር ላይ የተፈጸመ ታላቅ በደል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቆም ዘንድ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግና ወንጀለኞቹ በአሰቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ እንዲያደርግ በድር ኢትዮጵያ ጥያቄውን ያቀርባል። 

ትናንትና የተወሰኑ ፅንፈኛ ቡድኖች በሞጣና በጎንደር ሙሰሊሞች ላይ የፈፀሙት አሰነዋሪና ዘግናኝ ጥቃት እንዳመመን ሁሉ ዛሬ በተደጋጋሚ በአርሲ ንፁሀን ላይ የተፈፀመው ጥቃት ነገም እንዳይቀጥል ሁላችንም  እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድነት መቆም ይኖርብናል። 

በመሆኑም  ለመንግስት እና ለየጸጥታ አካላት ባስተላለፉት ይህ ግድያ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና የየደረጃው ኃላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ ድር ኢትዮጵያ በጥብቅ ያስገነዝባል። 

 በድር አለም ዐቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት 

June 5, 2026, Washington, DC