ማን ይተካቸው???

ቀን: 03/20/ 2021

In the Name of Allah, Most Gracious, Most Merciful

ማን ይተካቸው???

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለላለፉት አያሌ ዓመታት የታላላቅ ዑለሞች መፍለቅያ መሆኗ ይታወቃል። የዚህ ጥንካሬ ምንጭ እንደ ሌሎች ሙስሊም ሀገራት ጠንካራ ተቋም ኖሯት ወይም የተለየ ድጋፍ ተደርጎ ሳይሆን የሙስሊሙ በተለይ የገጠሩ ማህበረሰባችን ከዕለት ጉርሱ ቀንሶ እስክ ዛሬ ድረስ የኢልም ቅብብሎሹን ሳይቋረጥ እንዲቆይ ማድረግ በመቻሉ ነዉ። የሀገራችን ዑለሞችም ከሌላው ዓለም በተለየ ሚሊዮኖችን ከመሃይምንት በማላቀቅና በተቋም ደረጃ የሚሰጠውን እውቀት ያለምንም መሰረታዊ እገዛና እውቅና በብቸኝንትና በብቃት ተወጥተዋል። በዚህም መሠረት ራሳቸውን መስዋት አድርገው የሀገርን ኋላፊነት

በጫንቃቸው ተሸክመው ስመጥር ዑለሞችን ለዓለም አበርክተዋል።ነገር ግን ለክፍለዘመናት ሳይናወጥ እዚህ የደረሰዉ ሀገር በቀል የኢልም ቅብብሎሽና በብዙ ድካም ያነፃቸው ሀሪማዎች በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ተጋርጠውበት በመፍረስና ደረሳዎች በመመናመን ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም የዒልም ቅብብሎሹ የተወስኑ ግለሰቦች ወይም በጣት የሚቆጠሩ ድርጅቶች ኋላፊንት በቻ ሳይሆን ተቋሞቻችንን ማዘመንና ተተኪውን ትውልድ ማፍራት የሁሉም ሙስሊም ግዴታና ለነገ የማይባል አደራ መሆኑን በድር ኢትዮጲያ ያምናል።

ይህንን የተቀደሰ አላማ አንግበው ታላላቅ ዑለሞቻችን ግንባር ቀደም ሆነው በመምራት ላለፊት ጥቂት ዓመታት ያደረጉትን ጥረት በድር ኢትዮጵያ ያደንቃል። በተጨማሪ ሱና ኢስላማዊ እውቀትና የዓረብኛ ቋንቋ ኢንስቲትዩት ለሁለት (2) ወራትማን ይተካቸው?” በሚል የጀመረውን የገቢ ማሰባሰብ በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች፣ የበድር ኮሚኒቲዎች እንዲሁም ሌሎች ተቋማት በጋራም ሆነ በተናጠል እገዛ እንዲታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋልን።  በዚህ አጋጣሚ Ethiopian Scholars Support Charity (ESS Charity ) የተዘጋጀውን GoFundMe (https://www.gofundme.com/f/man-ytekachew?utm_campaign=p_lico+share-sheet&utm_medium=chat&utm_source=whatsapp-visit) በመቀላቀል ያቅማችሁን እንድትለግሱ በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

የበድር ኢትዮጵያ አለማቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት 

በድር ኢትዮጵያ          ሰሜን አሜሪካ                ማርች 20 2022

Leave a comment

All comments are moderated before being published