Official Announcements From Badr

የበድር ቦርድ ምርጫ ማካሄዱን ስለማሳወቅ

Posted by Badr Ethiopia on

የበድር ቦርድ ምርጫ ማካሄዱን ስለማሳወቅ

የበድር ቦርድ ምርጫ መካሄዱን ሰለማሳወቅ     የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በቦርድ የሚመራ ድርጅት ሲሆን ባለፉት ዓመታት በድርጅቱ ተከስተዉ በነበሩ ዉስጣዊና ዉጫዊ ችግሮች ሳቢያ ወቅቱን የጠበቀ ምርጫ ያልተካሄደ ቢሆንም በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ ምርጫዎችም ቢሆን በተወሰኑ አካላት የተደረገ ሽግሽግ እንደነበር ይታወቃል።    ሆኖም በ20ኛዉ የበድር ጉባኤ ወቅት ይደረጋል ተብሎ በእቅድ የተያዘዉ የቦርድ እና የስራ አስኪያጆች ምርጫ     በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አማካይነት ጉባኤዉ አለመካሄዱ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት እንደ ባህልም ሆኖ በድርጅቱ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ምርጫ መደረጉ ቀደም ሲል በነበረዉ ተለምዶ እየተከናወነ ቢዘልቅም ዘንድሮ ጉባኤዉ ባለመካሄዱ ምርጫዉም ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።      በአሁኑ ወቅት የኮምዩኒቲዎችም ሆነ የቦርድ አባላት ቁጥር ቀደም...

Read more →

መልካም ተግባር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል

Posted by Badr Ethiopia on

መልካም ተግባር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል

መልካም ተግባር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል    በሀገራችን ለረጅም ዘመናት መልስ ካጡ ጉዳዮች በከፊል ለዉጤት እየበቁ ወይንም ምላሽ እያገኙ መሄዳቸዉ አበረታች ተግባር በመሆናቸዉ ሊበረታቱ ይገባል እንላለን። በተለይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መሰረታዊ ጥያቄ ሆነዉ አስተዋሽ ተነፍጎአቸዉ ሲንከባለሉ የነበሩት ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎች ዋነኛዎቹ ናቸዉ።    በ2007 እኤአ የበድር ልዑካን ቡድን በበርካታ ጉዳዮች ጥናታዊ ጽሁፍ አዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ከፍተኛ አካላት ሲያቀርብ የፋይናንስ ተቋማትን በተመለከተ  “ ከሙስሊም ባህል አኳያ የተቀረጹ የፋይናንስ ተቋማትም አስፈላጊ በመሆናቸዉ ማደራጀት እና ከወለድ ነጻ የሆኑ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት ቢቋቋሙ ከሁሉም በላይ ወለድ ዉስጥ ላለመግባት ከኢንቨስትመንት የታቀቡ ዜሆችን በልማት ለማሳተፍ አይነተኛ ሚና ይኖራቸዋል ፤ ድህነትን ለመቀነስ የሚደረገዉ...

Read more →

በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍን ስለመጠየቅ

Posted by Badr Ethiopia on

በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍን ስለመጠየቅ

በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍን ስለመጠየቅ     በሀገራችን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለዉ የአንበጣ መንጋ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሰምተናል አይተናልም።       በተለይ በአማራ ክልል ወሎ አካባቢ የሚገኙ ቁጥራቸው በዛ ባሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች እንዲሁም የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአንበጣው መንጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉ አካባቢዎች ላይ  ሰብላቸው ከጥቅም ውጭ ሆኗል። የገበሬው ሁኔታ እንደምናዉቀው አመት ለፍቶ ጠብቆ የሚሰበስበው ሰብሉን አጥቶ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በችግር ላይ ይገኛል።    ምንም እንኳን ጥፋቱን ለመታደግ በቀላል የሚታሰብ እንኳ ባይሆንም መንግስት በደረጃዉ ይህን መሰል የሰብል ዉድመት ዳግም በሀገሪቱ እንዳይከሰት በቋሚነት ጥናት አድርጎ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቅረፍ እንደሚገባዉ ...

Read more →

ታዋቂዉ ዓሊም ሸይኽ መሐመድ ዓሊ አደም ወደ አኼራ ሄዱ

Posted by Badr Ethiopia on

ታዋቂዉ ዓሊም ሸይኽ መሐመድ ዓሊ አደም ወደ አኼራ ሄዱ

­­     ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ኢትዮጵያ ታዋቂዉን ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ አደምን አጣች    ኢትዮጵያዊዉ ታላቅ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ አደም ወደ አኼራ መሄዳቸዉን የሰማነዉ በታላቅ ሀዘን ነዉ። ኑሮአቸዉን በሳዑዲ ያደረጉ እዉቁ ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ለብቃታቸዉ በዓለም ደረጃ እዉቅናን ያገኙ ታላቅ ስመ ጥር ዓሊም ነበሩ። በርካታ የጻፉዋቸዉ ኪታቦች እንዳላቸዉም ይታወቃል ።    ሀገራችን ኢትዮጵያ ብርቅዬ ዓሊሞች ያሏት ቢሆንም በወጉ ሳንጠቀምባቸዉ በሀገር ዉስጥ በሚደርስባቸዉ አሉታዊ ተጽእኖ ሳቢያ እምነታቸዉን በአግባቡ ለመተግበር ሲሉ በየሀገራቱ በስደት ለመኖር እየተገደዱ ናቸዉ።    ዓሊሞቻችንን መጠበቅ የሁላችን ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ ልዩ ትኩረት መስጠት  እንደሚገባ እያሳሰብን በተለይ የሚመለከታቸዉ ክፍሎች በሁለንተናዊ መልኩ ተጠናክረዉ ለዉጥ ሊያመጣ በሚችል ሁናቴ ለዓሊሞቻችን ልዩ...

Read more →

የአረብኛ ቋንቋም ይታሰብበት እንላለን

Posted by Badr Ethiopia on

የአረብኛ ቋንቋም ይታሰብበት እንላለን

­­ የአረብኛ ቋንቋም ይታሰብበት እንላለን      በሀገራችን እየተከናወኑ ያሉ ለዉጦች አበረታች ከመሆናቸዉ አልፎ እየታዩ ያሉ ተግባራትም ሊመሰገኑ ይገባል የሚል እምነት አለን ። በቅርቡ በተለያዩ ክልሎች በትምህርት ቤቶች ደረጃ ሊሰጡ ይገባሉ በሚል የተለያዩ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ቋንቋዎችን በትምህርት ቤቶች ደረጃ ለመስጠት ቅድመ ሁኔታዎችን እያመቻቹ እንደሆነ መገለጻቸዉ ይታወቃል። ይህም ሂደት እጅግ በጣም አበረታች መሆኑን በመግለጽ ለአፈጻጸሙ ስኬታማነት ትኩረት ይሰጠዉ እንላለን ።      በተጨማሪነት ይሰጣሉ ተብለዉ ከተጠቀሱ ቋንቋዎች በተጓዳኝ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል የምንለዉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ የተናጋሪ ቁጥር ካላቸዉ ቋንቋዎች አንዱ የሆነዉ የአረብኛ ቋንቋ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ግን በተጨማሪነት ይሰጣሉ ተብለዉ ከተጠቀሱ ቋንቋዎች ዉስጥ አለመካተቱ እጅጉን አሳስቦናል።    በተለይ በሀገራችን...

Read more →