የአንዋር መስጂድ ምክትል ኢማም የነበሩት ሀጅ ሁሴን አሊ ወደ አኼራ ሄዱ

Posted by Badr Ethiopia on

 

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የአንዋር መስጂድ ምክትል ኢማም የነበሩት ሀጅ ሁሴን አሊ ወደ አኼራ ሄዱ

ሐጅ ሁሴን አሊ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ 01 (ሐራ አካባቢ) የተወለዱ ሲሆን እድሜያቸዉን በሙሉ በዲን ትምህርት ላይ ያሳለፉ ታላቅ አሊም ነበሩ። አላህ (ሱወ) ይዘንላቸዉ።

   በአዲስ አበባ በሚገኘዉ የታላቁ አንዋር መስጂድ ዉስጥ በቁርአንና በኪታብ ትምህርት ለሰላሳ ዓመታት በማስቀራት ታላቅ ስራ ያከናወኑና በርካታ ደረሳዎችን ከማፍራታቸዉ አልፎ ለዲነል ኢስላም መጠናከር የድርሻቸዉን የተወጡና ከታታላቅ አሊሞችም አንዱ የነበሩ ሲሆን በአንዋር መስጂድም ላለፉት አስራ አምስት ዓመታትም ምክትል ኢማም ሆነዉ ሲያገለግሉ ቆይተዋል። 

   በዛሬዉ እለት በ63 አመታቸዉ በድንገተኛ አደጋ ወደ አኼራ መሄዳቸዉን  መስማት በኡማው ታላቅ ሀዘን ፈጥሯል። አላህ (ሱብሁዋነዉ ወተአላ) የአኼራ ቤታቸዉን እንዲያሳምርላቸዉና ጄነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸዉ ዘንድ አላህን እየተማጸን ለቤተሰቦቻቸዉና ለሙስሊሙ ኡማ መጽናናትን በመመኘን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻላነ።

በቅርብ ወራቶችም በርካታ ኡለማዎቻችንን በሞት አጥተናል ። ለቀሪዎቹ ረጅም እድሜና ጤናን እንመኛለን።

በድር ኢትዮጵያ      ሰሜን አሜሪካ      አፕሪል 20 2021               

       


← Older Post Newer Post →