አንገት የሚደፋበት ዘመን ላይ አይደለንም !!!

Posted by Badr Ethiopia on

    ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ በተደጋጋሚ ወቅቶች በጠብ ጫሪነት የሚፈጸሙበትን ትንኮሳዎችን በአብሮ በመኖር እሳቤና በዜጋዊ ሀላፊነት በትእግስት ማሳለፍና አገርን የሚያህል ታላቅ ራዕይ አሻግሮ በማየት ህልዉናዉ እንዳይናጋና አንድነታችን ተጠብቆ ማለፍን በድር ኢትዮጵያ በሰከነና ጥበብ በተሞላበት ባህላዊና ሀይማኖታዊ አደብና እሴቶቻችንን ጠብቀን በመመራት በሰላም አብሮ መኖርን ሲሰብክ ኖሮዋል።

   በዚህ በተቀደሰና በተከበረ የረመዳን ወር ብሎም በቀሩት ወርቃማ የመጨረሻዉ ቀናቶች የበለጠ ወደ አላህ (ሱብሁዋነሁ ወተአላ) ለመቃረብ በጸሎትና በስግደት በምናሳልፍበት ወቅት ዜግነታዊ መብቶቻችንን የጋራ የሀገርና የአካባቢ እሴቶችን ባለቤትነትን የሚገፍ ዉሳኔ በመፈጸሙና በሕዝብ አደባባይ ያዉም ከሀገሪቱ ከፍተኛዉን ቁጥር በያዘዉ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲሁም በሙስሊሙ የግብር ገንዘብ በተሰራዉ አደባባይ ላይ መሰብሰብ አትችሉም መባሉ የመንግስት እና የቤተክርስቲያን ግንኙነት  ምን ላይ እንደሆነ እሳስቦናል። ሙዚቀኛ በሚደንስበት አደባባይ ፤ ሰልፎችበሚካሄዱበት አደባባይ ፤ የዉጭ ሀገር ዜጎች በሚያዘወትሩበት ቦታ ፤ የእሬቻ በዓል በተክበረበት የሀገር ሀብት ሙስሊሙማህበረሰብ እንዳይጠቀምበት ማገድ ከፖሊሲ ችግር አልፎ ብዙ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ማሰብን ይሻል።

   በሀገሪቱ ያለዉ የእዝሰንሰለት የመንግስት ከፍተኛ አካላት፤ የፓርላማ አባላት፤ የሀገር አስተዳደር፤ የሰላም ሚኒስትር፤ ፖሊስ ኮሚሽነር እና መሰልተቋማት ባሉበት ሀገር አንዱ የወሰነዉን ሌላዉ የሚያፈርስበት ስነ ስርአት ብሎም መናበብ የጎደለዉ አመራር እንዴት ሊከሰት ቻለ?

   በቅርቡ የኢትዮጵያእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በመንግስት ጭምር እዉቅና ተጠርቶ በነበረበት ወቅትም የሀይማኖት አባቶች(ኡለማዎቻችን) በተከራዩት ሆቴል ጉባኤአቸዉን እንዳያካሄዱ በመንግስት የደረሰባቸዉ መጉላላት ከፍተኛ ሀዘኔታን መፍጠሩ እየታወቀዳግም የዜግነት መብቱ ተጥሶ በሕዝብ አደባባይ በጎዳና ከሚገኙ የማህበረሰብ አካላት ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም  ለማከናወን አስፈላጊዉን ፈቃድና ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ በመጨረሻዉ ሰዓትፕሮግራሙ መታገዱና በጭስ እንዲበተን መደረጉ ከበደል አልፎ ሀጢአትም ነዉ።

   በድር ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ይህን መሰል ህገመንግስታዊ ጥሰትንና ተግባሮችን በጥብቅ ይኮንናል። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም እንደእምነት ተቋም ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉንና የሚጠበቅባቸዉን የግላቸዉን ከመወጣት አልፈዉ በሙስሊሙ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቷያለችበትን አጣብቂኝ ለግል ጥቅም በማዋል ሽብር በመንዛት መሰል እንቅስቃሴዎችን በማራመድዋ ለጥፋቱ ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናትምእንላለን። የክርስትና እምነት ተከታዮችም ሂደቱ አግባብ አለመሆኑን በመቃወም ሀቁን  ላሳያችሁና ድጋፍ ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነዉ።

  የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ ወጣቶች በዚህ የግፍ ተምሳሌትበሆነና ከህገ-መንግስቱ ድንጋጌ ውጭ በሆነ ውሳኔ አመጽ ሲፈጸምባችሁ ላሳያችሁት ትዕግስትና የአገር ወዳድነት አላህ የላቀውን ክብርናሞግሰ እንዳላበሳችሁ ልንግልጽላችሁ እንወዳለን። በድርኢትዮጵያም የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ከሚመለከታቸዉ አካላት በቀጣይ ልዩ ክትትል የሚያደርግ መሆኑንእንገልጻለን።  

በድር ኢትዮጵያ  ሰሜን አሜሪካ   ሜይ 9 2021                                          


← Older Post Newer Post →