ታላቁ ዓሊም ሼህ ሂዝቡላ መሀመድ አሚን ወደ አኼራ ሄዱ

Posted by Badr Ethiopia on

  ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

   የሀገራችን ታላቁ አሊም ሼህ ሂዝቡላህ መሀመድ አሚንበትላንትናዉ እለት ወደ አኼራ መሄዳቸዉ ተሰምቷል። በራያ የተወለዱና እድሜያቸዉን በሙሉ ለእስልምና በዳዕዋ ሲያገለግሉ የቆዩታላቁ አሊም እንደነበሩና ኑሮአቸዉንም በትዉልድ ቀዬአቸዉ እንደነበር ይታወቃል። 

   ሼህ ሂዝቡላህ ዲናቸዉን ለማስፋፋት ባደረጉት ጥረትሁሉ በየዘመናቱ በርካታ እንግልት እና እስሮችን ያስተናገዱ ቆራጥ እና የተብቃቁ አሊም ነበሩ። 

   በቅርቡ በመጅሊስ በተጠራዉ የጠቅላላ ጉባኤ ላይለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያሉም መንገድ ላይ ለእስር መዳረጋቸዉ ምን ያህል ተጽእኖ ይደረግባቸዉ እንደነበርየሚያሳይ ሲሆን እሳቸዉም ችግሮቹን ሁሉ ተቋቋሙዉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የኡለማ አባል እንደ መሆናቸዉመጠን ስብሰባዉን ለመታደም በቅተዋል።

   የመጅሊሱን ተቋማዊ ለዉጥ ለዉጤት ለማብቃት በአዲስ አበባበተጠራዉ የመጅሊሱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ በኋላ ምክር ቤቱ ያሳለፋቸዉን የዉሳኔ ሀሳቦች በመንግስት በኩል እዉቅናናተቀባይነት እስከሚያገኙ ድረስ ሁሉም የምክር ቤቱ የኡለማ አባላት አዲስ አበባ እንዲቆዩ በተስማሙት መሰረት እሳቸዉም በዚያዉየቆይታ ጊዜያቸዉ በህመም ወደ አኼራ ሄደዋል። አላህ (ሱብሁዋነሁ ወተአላ) ጄነተል ፊርዶስ ይወፍቃቸዉ፤ የሰሩዋቸዉ መልካምስራዎች ሁሉ የአኼራ ቤታቸዉን እንዲያሳምርላቸዉ አላህን እየተማጸን ቤተሰቦቻቸዉ እና ለመላዉ ኢትዮጵያ ሙስሊም መጽናናትንእየተመኘን በድር ኢትዮጵያም በሼህ ሂዝቡላህ መሀመድ አሚን ዜና ህልፈት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

በድር ኢትዮጵያ      ሰሜንአሜሪካ      አፕሪል 11 2021        


← Older Post Newer Post →