የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድን የኢድ አልፈጥር በአል አከባበርን አስመልክቶ ከበድር ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ዲያስፖራና ለጠቅላላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ህብረተሰብ ኢድ አልፈጥርን በአንድነትና በድምቀት በመዲናችን አዲስ አበባ እንድናከብር ያድርጉልን ጥሪ  ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ልብ አሙዋቂ ፣ወቅቱን የዋጀ አስደሳች ዜና ነው።

በድር ኢትዮጵያ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም በተለይ የዲያስፖራው ሙስሊም ይህን በጎ አጋጣሚ በመጠቀም አንድነቱን አፅንቶ አምና ያዘጋጀውና አድናቆትን አትርፎ ሬኮርድ ሰብሮ የነበረውን የኢፍጣር ፕሮግራም በመድገምና ይህንንም የኢድ በአል በኅብረትና በድምቀት እንዲያከብር የበኩሉን ድጋፍ ያደርጋል።

ኢትዮጵያ አገራችን ብዙ እምነትና ባህል፣ በአላትና ድንቅ ታሪካዊ ቦታዎች ያላት አገር ናት። የተለያዩ የእምነት በአላትን ደመቅ አድርጎ ማክበር የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር ከማድረጉም በላይ ያለንን እምቅ ክህሎትና አብሮ የመኖርን ዘይቤን ለአለም ህዝብም ያስተዋዉቃል።    

ስለዚህ ይህ የተደረገው የክቡር ዶክተር ዓቢይ ጥሪ አዎንታዊና አመርቂ ውጤት እንደሚኖረው ጥርጥር የለንም። 

በዚህ አጋጣሚም ለተደረገልን ጥሪም ክብርና ምስጋናችንን እንገልፃለን። በድር ኢትዮጵያ በየአመቱ ሲያደርግ የነበረውንና የዘንድሮውን የ2022 ጉባኤውን ከጁላይ 15-25በአዲስ አበባ ያኪያሂዳል። 

ስለዚህም ለዲያስፖራው ሙስሊም ሁለት እንቁ እድሎች የተፈጠሩለት ሲሆን እነዚህን አጋጣሚዎች አገርን በመጎብኘትና በመደገፍ ፣ዘመድንና ወገንን በመርዳት ፣ከሁሉም በላይ የአገሩን ገፅታ በመቀየርና በማደስ ጥሩ የእረፍትና የመመካከሪያ አጋጣሚ እንዲያደርገው በድር ኢትዮጵያ ያሳስባል።ለዚህም ስኬት በድር ኢትዮጵያ ሁሉም የበድር አባል ኮሚኒቲዎችና ደጋፊዎች ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

 

 

በድር ኢትዮጵያ ሰሜን አሜሪካ

ፌብሩዋሪ 23/2022

Leave a comment

All comments are moderated before being published