በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍን ስለመጠየቅ

በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍን ስለመጠየቅ

    በሀገራችን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለዉ የአንበጣ መንጋ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሰምተናል አይተናልም።   

   በተለይ በአማራ ክልል ወሎ አካባቢ የሚገኙ ቁጥራቸው በዛ ባሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች እንዲሁም የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአንበጣው መንጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉ አካባቢዎች ላይ  ሰብላቸው ከጥቅም ውጭ ሆኗል። የገበሬው ሁኔታ እንደምናዉቀው አመት ለፍቶ ጠብቆ የሚሰበስበው ሰብሉን አጥቶ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በችግር ላይ ይገኛል።

   ምንም እንኳን ጥፋቱን ለመታደግ በቀላል የሚታሰብ እንኳ ባይሆንም መንግስት በደረጃዉ ይህን መሰል የሰብል ዉድመት ዳግም በሀገሪቱ እንዳይከሰት በቋሚነት ጥናት አድርጎ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቅረፍ እንደሚገባዉ  አጠንክረን እያሳሰብን እኛም ለወገኖቻችን ወቅታዊ ችግርን ለማስታገስ በሚያስችል ደረጃ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅብን በማመን ነዉ ። 

   ይህንኑ ወቅታዊ የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ ሁሉም ማህበረሰብ ሊረባረብበት የሚገባ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ የማያጠራጥር ቢሆንም በበድር ሥር የምትገኙ ኮምዩኒቲዎችም ሆነ ሌሎች ለተጎዱ ወገኖቻችን መርጃ የሚሆን የገንዘብ አሰባሰብ ሊደረግ እንደሚገባ ታምኖበታል።

     በመሆኑም ወገንን በመታደግ ተግባር አሻራችሁን ለማሳረፍ እንድትችሉ እንደ አቅማችን በመሳተፍ ለዉጥ እናመጣ እያልን በኮምዩኒቲዎች ደረጃም የገንዘብ አሰባሰብ ጥረት በማድረግ ከአጣፊነቱ የተነሳ እንደአመቺነቱ በናንተ በኩል መላክ የምትችሉ ሲሆን በናንተ በኩል መላክ የማያስችላችሁ ሁኔታ ካለ በበድር በኩል ሊላክላችሁ እንደሚችልም ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።

  አላህ (ሱብሀንሁ ወተአላ) ሀገራችንን ከድህነት ይጠብቅልን !!

በድር ኢትዮጵያ       ሰሜን አሜሪካ      ኦክቶበር  11 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published