ታዋቂዉ ዓሊም ሸይኽ መሐመድ ዓሊ አደም ወደ አኼራ ሄዱ

­­     ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

ኢትዮጵያ ታዋቂዉን ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ አደምን አጣች

   ኢትዮጵያዊዉ ታላቅ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ አደም ወደ አኼራ መሄዳቸዉን የሰማነዉ በታላቅ ሀዘን ነዉ። ኑሮአቸዉን በሳዑዲ ያደረጉ እዉቁ ሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ለብቃታቸዉ በዓለም ደረጃ እዉቅናን ያገኙ ታላቅ ስመ ጥር ዓሊም ነበሩ። በርካታ የጻፉዋቸዉ ኪታቦች እንዳላቸዉም ይታወቃል ።

   ሀገራችን ኢትዮጵያ ብርቅዬ ዓሊሞች ያሏት ቢሆንም በወጉ ሳንጠቀምባቸዉ በሀገር ዉስጥ በሚደርስባቸዉ አሉታዊ ተጽእኖ ሳቢያ እምነታቸዉን በአግባቡ ለመተግበር ሲሉ በየሀገራቱ በስደት ለመኖር እየተገደዱ ናቸዉ።

   ዓሊሞቻችንን መጠበቅ የሁላችን ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ ልዩ ትኩረት መስጠት  እንደሚገባ እያሳሰብን በተለይ የሚመለከታቸዉ ክፍሎች በሁለንተናዊ መልኩ ተጠናክረዉ ለዉጥ ሊያመጣ በሚችል ሁናቴ ለዓሊሞቻችን ልዩ ትኩረት በሀገር ዉስጥ ያሻቸዋልና ይታሰብበት በማለት ለመጠቆም እንወዳለን ። 

  በድር ኢትዮጵያ በሸይኽ ሙሐመድ ዓሊ ዜና ህልፈት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ነፍሳቸዉን አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) በጀነተል ፊርደውስ ያኖራቸዉ ዘንድ እየተማጸን ለቤተሰቦቻቸዉ እንዲሁም ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን ።   

 አላሁ አክበር

በድር ኢትዮጵያ   ሰሜን አሜሪካ    ኦክቶበር 8 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published