ለአፋር ክልል ድጋፍን ስለመጠየቅ

ለአፋር ክልል ድጋፍን ስለመጠየቅ

    በሀገራችን በጣለዉ የክረምት ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ ወንዞች ከሚፈለገዉ በላይ በመሙላታቸዉ የተነሳ ፍሰታቸዉ አቅጣጫውን በመቀየር በአብዛኛዉ ሜዳማ ተፋሰስ ባላቸዉ የሀገሪቱ ክልሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ይታወቃል።

   በተለይ በአፋር ክልል የሚገኙ ዜጎች ኑሮአቸዉ በእርሻና በከብት እርባታ ላይ ብቻ የተመሰረተ ከመሆኑ አንጻር በአካባቢዉ በዝናቡ ከፍተኛ ጎርፎች በመፈጠራቸዉ የእርሻ መሬታቸዉ በዉኋ ከመጥለቅለቁ አልፎ ከብቶቻቸዉም በሚያሳዝን መልኩ በጎርፍ ተወስዶባቸዋል፤ በርካቶችም ተፈናቅለዋል።

   ይህንኑ ወቅታዊ ችግራቸዉን ለመቅረፍ ሁሉም ማህበረሰብ ሊረባረብበት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ የማያጠራጥር ቢሆንም በበድር ሥር የምትገኙ ኮምዩኒቲዎችም ሆነ ሌሎች ለተጎዱ ወገኖቻችን ማቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ አሰባሰብ ሊደረግ እንደሚገባ በማመን ለዚህም ወገንን በመታደግ ሥራ አሻራችሁን ለማሳረፍ እንድትችሉ በመሳተፍ እንቅስቃሴዉን እንድታፋጥኑ እያስታወስን በኮምዩኒቲዎች ደረጃም የገንዘብ አሰባሰብ ጥረት በማድረግ ከአጣፊነቱ የተነሳ እንደአመቺነቱ በናንተ በኩል መላክ የምትችሉ ሲሆን ለአላላክ ችግር የሚያጋጥማችሁ ኮምዩኒቲዎችም ካላችሁ በበድር በኩል ሊላክላችሁ እንደሚችልም ልንገልጽላችሁ እንወዳለን።

አላህ (ሱብሁዋነሁ ወተአላ ) ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን

በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ     ኦገስት 9 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published