አሳዛኙ የግፍ ግድያ በኢማሞቻችን ላይ ተካሄደ

አሳዛኙ የግፍ ግድያ በኢማሞቻችን ላይ ተካሄደ

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ተነጥሎ እየተፈጸመበት ያለው በደል ብሎም አሰቃቂ ግድያ ዳግም ማየቱ እጅግ በጣም ያሳዝናል፤ ያበሳጫልም። ከሁሉም የሚገርመዉ ግን በመኖሪያ ቤታቸዉ ሆነዉ ሳለ በታጠቁ የመከላከያ ሀይላት በግፍ የመገደላቸዉ ሁኔታ ግን ይበልጥ ዉስብሰብ አድርጎታል።   

   በምዕራብ አርሲ ዞን ሃሳሳ ወረዳ  ኢማሙን ጨምሮ  ከነቤተሰባቸዉ በታጠቁ ሀይሎች በግፍ ተገድለዋል። አላህ (ሱብሁዋነሁ ወተአላ) ጄነተል ፉርዶስን ይወፍቃቸው ፤ አሜን 

   በከተማዉ የሚገኘዉን መስጂድ ሰብሮ በመግባት ምክትል ኢማሙን በጥይት ከማቁሰላቸዉ አልፎ ኢማሙንም በግል መኖሪያ ቤታቸዉ ዉድ ባለቤታቸዉ እና ልጃቸዉን ጨምሮ በታጠቁ የመንግስት አካላት የመገደላቸዉ ጉዳይ እንቆቅልሽ ሆኖብናል፤ ምን አይነት አረመኔያዊነት እንደሆነ መተንበይም አጠራጣሪ የሚያደርገዉ ነገር የለም።

       የሚፈለጉበት ጉዳይ እንኳ ቢኖር በህግ ጥላ ስር አዉሎ ማጣራትና ህጋዊነትን በተላበሰ መልኩ ፍትህ መስጠት ሲገባ በትጥቅ ትግል እንደሚፋለም ሰዉ የግል መኖሪያ ቤታቸዉን ጦር ሜዳ በማስመሰል ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር በተቀመጡበት ለተፈጸመባቸዉ አሰቃቂ ግድያ በድር ኢትዮጵያ እጅግ በጣሙን  ሲያወግዝ ለሚቀርቡ ማንኛዉም ዓይነት ማስተባበያዎችም ተቀባይነት እንደሌላቸዉ በማሳወቅ ነዉ።

    ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የፈጸሙ አካላት በአስቸኳይ ተለይተዉ ለህግ እንዲቀርቡ እና ሂደቱም በመንግስት ሚዲያ ለህዝብ በግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥበት አጥብቀን እየጠየቅን ሟቾቹን አላህ ነብሳቸዉን በገነት ያኑራቸዉ እያልን ለቤተሰቦቻቸዉና ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ መጽናናቱን እንመኛለን።

   አላሁ አክበር

በድር ኢትዮጵያ         ሰሜን አሜሪካ        ኦገስት 20 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published