በስልጢ ዞን የጎርፍ አደጋ ተከሰተ

በስልጢ ዞን የጎርፍ አደጋ ተከሰተ

         በዘንድሮ ዓመት በሀገራችን በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ ከሚወድመዉ ንብረት ባሻገር በርካታ ዜጎች ከቀዬአቸዉ መፈናቀላቸዉ ሲሆን በተለይ በአፋር ክልል ለተፈጠረዉ ዉድመት እኔም አፋር ነኝ በሚል መርሀ ማህበረሰቡ እያደረገ ያለዉ ድጋፍ እጅግ በጣም አበረታች ነዉ። ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም እያልን ችግሩ በተጨማሪነት በደቡብ ክልል ዉስጥ በሚገኘዉ የስልጢ ዞንም ባለፉት ዓመታትም በተመሳሳይ ወቅት ጎርፍ ከሚያጠቃቸዉ አካባቢዎች አንዱ እንደሆን የሚታወቅ ሲሆን በዘንድሮዉም ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋርጦበታል።  

     በቅርብ ጊዜያት ከኮቪድ 19 ጀምሮ ማህበረሰቡን ለተለያዩ ድጋፎች ማስቸገራችን የሚታወቅ ነዉ። አንዱ ችግራችን ሳይቀረፍ ሌላዉ እየተተካብን ይገኛል። ይህም የሚያሳየዉ ብዙ ያልተሰሩ ነገሮች እንዳሉ እና በተለይ በዲያስፖራ የምንገኝ ማህበረሰብ ሀገር ዉስጥ ከሚገኘዉ ህዝብ ይልቅ በመጠኑም ቢሆን በኢኮኖሚ ልንሻል ስለምንችል ጥያቄዎች ሊደራረቡ ይችላሉና አላህ በሰጠን ሀብት እና አቅም ሌላዉን ለመርዳት እጃችንን መዘርጋቱ ሁሌም ይጠበቅብናል።

       ስለዚህ ለአፋር ከምናደርገዉ መዋጮ ጎን ለጎን የስልጢ ማህበረስብም እርዳታችንን ይፈልጋልና   በየኮምዩኒቲዎች የተለመደዉን ጥረታችሁን ስንጠይቅ ከይቅርታ ጋር ሆኖ እንደምታሳኩትም በመተማመን ጭምር ነዉ።

አላሁ አክበር

በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ    ኦገስት 20 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published