በአባይ ወንዝ የዘመናት ምኞትና ስኬት

 በአባይ ወንዝ የዘመናት ምኞትና ስኬት 

      ሀገራችን  ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዉሀ ሀብት ባለቤት ብትሆንም ለራሷ አገልግሎት ሳይሰጥ ሌሎች ሀገራትን በማልማት ፤ በማበልጸግና ለተለያዩ አገልግሎት ሲጠቅም በኛ ሀገር ግን ታዋቂዉ የአባይ ወንዝን በተመለከተ ለአባባል ብቻ “አባይ ማደሪያ የለዉ ግንድ ይዞ ይዞራል” በሚል እንደመልካም ነገር በስርዐተ ትምህርት ተካቶ ከመነገሩ ዉጭ ፋይዳ ያልነበረዉ በሚመስል መልኩ ይተረክ የነበረዉ በዘመናችን በህዳሴ ግድቡ መፍትሄ አግኝይቶ ለመቋጨት በቅቷል። 

     የህዳሴ ግድቡ በአባይ ወንዝ ላይ በቅድሚያ ለሀይል ማመንጫነት በሚል በተያዘዉ ፕሮግራም መሰረት በአስር ዓመቱ ግድቡ ለመጀመሪያ ዙር የዉሀ ሙሌት መብቃቱ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በትዊተር ገጻቸዉ መግለጻቸዉ እጅጉን አስደስቶናል። ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።

    የህዳሴ ግድቡ በሌሎች የዉጭ አካላት በኩል ሊፈጥር የሚችለዉን ተጽዕኖ ከጅምሩ ግምት ዉስጥ በማስገባት ለግንባታዉ የሚያስፈልገዉን ሙሉ ወጪ በሀገር በቀል ደረጃ ከህብረርተሰቡ በኩል በነፍሰወከፍ ወጪ ሆኖ ተፈጻሚ እንዲሆን ማድረጋቸዉ አስተዋይነት የተሞላበት ሂደትም ነበር። ምስጋና ይድረሳቸዉ።    

      የህዳሴ ግድቡ የመጀመሪያ ዙር የዉሀ ሙሌት በራሱ ታላቅ ብስራት ቢሆንም በቀጣይ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን አካቶ ሀገራችንን በተሻለ የእድገት ጎዳና እንድትገኝ መንግስት ተጨማሪ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ በመተማመን ነዉ።

     በመጨረሻም የዛሬዉን ቀን እዉን ለማድረግ ሌት ተቀን በብቁ አመራር ፤ በገንዘባቸዉ ፤ በእዉቀታቸዉ ፤ በሀሳባቸዉ፤ በጊዜያቸዉ እና በመሰል ሁኔታዎች ሁሉ ለተሳተፉና ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ሉአላዊነት ዉጤት ላይ ላበቁ ሁሉ በድር ኢትዮጵያ እጅግ በጣም የከበረ ምስጋና እያቀረበ በሚቻለዉ ሁሉ ከጎናችሁ እንደሚቆም በዚህ አጋጣሚ እያረጋገጥን ሀገራችንም ከአሁን ካለችበት ፈታኝ ወቅት ወጥታ በህዝቦቿ አንድነት ሰፍኖ ሰላሙን ያመጣልን ዘንድ አላህ (ሱወ) እንማጸናለን።

በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ     ጁላይ  22, 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published