በሃገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመብቱ ጉዳይ ከመንግስት ጋ ቁጭ ብሎ ጥያቄዎቹን ያቀረበውና የተወያየው እ፣አ፣እ፣2007 በወቅቱ ከነበሩት ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ነበር።

ይህም የሆነው በድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በላከው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አማካኝነት ሲሆን ይህ አጋሚ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ለሃገራችን ገፅታ የራሱን አሻራ ጥሎ አልፏል። በድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴ ወቅት የተነሱ ጥያቄዎች በወቅቱ ከይፈፀምላችኋል ቃል በዘለለ መልስ ያልተሰጠባቸው የዚያን ጊዜ የቀረቡ ጥያቄዎች የሚከተሉት ነበሩ። 

 1. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት /መጅሊስ/ በአዲስ መልክ ይዋቀር፤ ሙስሊሙ ያመነባቸውና የወከላቸው አካላትም በአመራር ላይ ይቀመጡ፤
 2. በሕገ-መንግስቱ የተቀመጡ የዜጎች መብቶችና የኃይማኖት እኩልነት ተፈጻሚ ይሁንልን፤
 3. ሀገራችን በእስልምና ኃይማኖት ካላት ልዩ ቦታ ተጠቃሚ ትሆንና በዚህም ምክኒያት ለአለም ሰላም የሚኖራት አስተዋፅዖ ይጎለብት ዘንድ መንግስት አስፋላጊውን ጥረት ያድርግ፤
 4. መንግስታዊ ያልሆኑ እስላማዊ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ያለልዩ ተፅንዖ እንድንቀሳቀሱ ይሁን፤
 5. የሀገሪቱን ሴኩላር አስተዳደር የሚጻረሩ አሰራሮች ይወገዱ፤
 6. የተዛባው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ቁጥር ይስተካከል፤
 7. የዜጎችን እምነትና ባህል ያገናዘበ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ገቢራዊ ይሁን፤
 8. የኃይማኖት ነክ ጉዳዮች በሚኒስትር ደረጃ ይቋቋም ዘንድ ሃሳብ እናቀርባለን፤ 
ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የኢስላሚክ ባንክ ምስረታና የመጅሊስ በአዋጅ መፅደቁ በጣም ደስ ብሎናል።
ለዚህ ሁሉ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን።
ይህን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ለማወቅ ይህንን ሊንክ ይጫኑ
 1. AXUM
 2. HARAR
 3. JIMMA
 4. MAKALE
 5. NEJASHI
 6. HAWASSA
 • Delegation's Report
 • The outcomes
 • Photo Gallery
 • Interviews
  • Leave a comment

   All comments are moderated before being published