በጉጉት ሲጠበቅ የነበረዉ ታሪካዊዉ የኡለማዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ

  የዛሬዉ ስኬት የእምነቱ ባለቤቶች የሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን የመላዉ የሀገራችን ህዝቦች ስኬት ነዉ ብለን እናምናለን። የአንድ ሀገር አንድነት ሰላምና እድገት የተሟላ ሊሆን የሚችለዉ ህዝቦች በሙሉ አቅምና ቅንነት በእኔነት ስሜት ሲሳተፉበት ብቻ ነዉ።

   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ አማካይነት የተዋቀረዉ ዘጠኝ አባላት ያሉት የተቋማዊ ለዉጥ ኮሚቴ       የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን (መጅሊስ) ለማሻሻልና ለማዋቀር ተዘጋጅቶ በቀረበዉ ሰነድ ላይ የኡለማዎች ጉባኤ ዛሬ ሚያዝያ 23 2011 የተካሄደዉና ባማረ መልኩ ተጠናቀቀዉ ጉባኤ እጅግ መደሰቱን በድር ኢትዮጵያ እየገለጸ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት በሙስሊሞች መሃከል የሚፈጠር የሰላም ፤ የአንድነትና የፍቅር ስሜት በሌሎች የሃገራችን ህዝቦች ዘንድ ለመፍጠር የሚኖረዉ አስተዋጾ ቀላል አይሆንምእንዳሉት ሁሉ እኛም ትክክለኛነቱን በተግባር ጠብቀን ልናቆየዉ የሚገባ ሲሆን ዶ/ር አቢይ አህመድም ቀናነላሳዩት ዉጤታማነት በህዝበ ሙስሊሙ ስም ምስጋናችን የላቀ እንደሆነ ልንገልጽ እንወዳለን።  

   አንድ ሃገር የህዝቦቿን አኩል ተጠቃሚነትን ለማስፈን መጣር እንዳለባት ሁሉ ህዝቦቿም ባላቸዉ አቅምና እዉቀት ሀገራቸዉን ወደፊት የማስኬድ ብሎም የማበልጸግ ኃላፊነት እንዳለባቸዉ በድር ኢትዮጵያ በጽኑ ያምናል። በመሆኑም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ተጋርጦበት ከነበረዉ የክፍፍል እና የጠላትነት ስሜት ተላቆ በሃገር ግንባታና በለዉጡ ዘላቂነት ላይ በሙሉ ልብ በመሳተፍ ግዴታዉን በሁሉ መስክ ለመወጣት በቀጣይ ጥረቱን እንዲያጠናክር ለመጠየቅ እንወዳለን ።

    በመጨረሻም ለዛሬዉ ቀን መሳካት የድርሻችሁን የተወጣችሁ ሁሉ አላህ ምንዳችሁን ያብዛዉ እያለ በድር ኢትዮጵያ በእህት ድርጅቶችና በአባላቱ ስም ደስታዉን ለመግለጽ ይወዳል። ይህ ዛሬ የታየዉ የአንድነት ስሜት ማዝለቅ እያንዳንዱ ሙስሊም ግዴታዉ መሆኑን አዉቆ እንዲንከባከበዉ አደራ እያልን በድር ኢትዮጵያም ለወደፊቱ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

አላሁ አክበር !!

በድር ኢትዮጵያ        ሰሜን አሜሪካ        ግንቦት 1 2019   

 

Leave a comment

All comments are moderated before being published