የሀዘን መግለጫ
አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ዘመናት በተለያዩ ዘርፎች የገጠሟትን ከፍተኛ ፈተናዎች በጽናት ተጋፍጣ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሳለች። ህዝባችን ለተሻለ ለዉጥና ዲሞክራሲ ባደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትግል ሳቢያ በመጣዉ ለዉጥ ወደፊት የመጣዉ የለዉጥ ቡድን በሚሰጠዉ አመራር የሚያኮሩ፤ የሚታዩ ፤ የሚጨበጡ ለዉጦችን በማየት ላይ እና ተዳፍኖ የነበረዉን ዲሞክራሲ በመለማመድ ላይ እንገኛለን።
በዚህ እጅግ አበረታችና ተስፋ ሰጪ የለዉጥ ጎዳና ላይ እያለን ህዝባችንን ያስደነገጠ አገራችንንም በከፍተኛ ፈተና ላይ የጣለ አሳዛኝ ክስተት ቅዳሜ ሰኔ 15/2011 ተፈጽሟል። በዚህ መንግስትን በሃይል የመገልበጥ ሙከራ በተባለዉ አደጋ ምክንያት ሀገራችን ፈተና ላይ ወድቃለች ፤ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችንም አጥታለች ።በድር ኢትዮጵያ ሀገራችን በገጠማት ችግር እንዲሁም ለሞቱ እና ለቆሰሉ ከፍተኛ የመንስት ባለስልጣናት የተሰማዉን ከፍተኛ ሃዘን ለመግለጽ ይወዳል።
ይህ ወቅት እጅግ ቅስም የሚሰብር ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በያለበት ያስደነገጠና ያሳዘነ ቢሆንም እኛ ኢትዮጵያዊያን በብሄር በሀይማኖት ሳንከፋፈል እጅ ለእጅ በመያያዝ አገራችን ላይ ያንዣበበዉን ከፍተኛ አደጋ ከመንግስት ጎን በመሆን በጋራ መሻገር እንችል ዘንድ በድር ኢትዮጵያ ጥሪዉን ያስተላልፋል።
አገራችን ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት ፈተና የምንታደጋት በፍቅር፤ በትብብር እና በአንድነት ተደጋግፈን ስንቆም ብቻ መሆኑ በድር ኢቶጵያ በጽኑ ያምናል። በዚህ አጋጣሚ የሀይማኖት አባቶች ፤ ያገር ሽማግሌዎች ፤ አባገዳዎች እና ምሁራን በዚህ ወሳኝ ወቅት ህዝቡን በማስተባበር እና በማረጋጋት ህዝባችን ለአገሩ ዘብ ይቆም ዘንድ የምታደርጉት አስተዋጾ እጅግ ወሳኝ ነዉና ይህንኑ ተግባር የበለጠ አጠናክራችሁ ትሰሩበት ዘንድ በድር ኢትዮጵያ ጥሪዉን በአክብሮት ያስተላልፋል።
በመጨራሻም ለሟች ቤተሰቦች እና ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን እየተመኘን አገርራችን ኢትዮጵያየጀመረችዉን ሁሉን አቀፍ ለዉጥ በቁርጠኝነት እንደምታስቀጥልናህዝቦቿም በሰላም ወጥተዉ የሚገቡበት የሰላም አየር የሚተነፍሱባት የሚሚገጥሟትን እንቅፋቶች ሁሉ በጽናት የምትሻገር እገር አሏህ ያደርጋት ዘንድ የዘወርት ፏችን ነዉ።
አሏህ አገራችንን እና ህዝቦቿን ይጠብቅ
በድር ኢትዮጵያ ሰሜን አሜሪካ ጁን 26 2018