ሀገራችን ኢትዮጵያውያ ለረዥም ዓመታት በዓለም ላይ ከምትታወቅባቸው እሴቶቿ መካከል ተቀዳሚውን
ስፍራ የሚይዘው አንድነትን አጎልብቶ ልዩነትን አጥብቦ ተሳስቦ በጋራ አብሮ መኖርን ነው። ሰሞኑን የተከሰተው አሳዛኝ ሁኔታ ይህን ለዘመናት ያጋመደንን ወገን ለወገኑ የሚለውን ብሂላችንን የሚጻረር መሆኑ አያጠያይቅም።
ስለዚህ ሁለም የሚያምረው በሃገር ላይ ሰላምና መረጋጋት ሲኖር ስለሆነ የአመለካከት ልዩነቶችን በዉይይት እየፈታን ሁላችንም አማራጭ ለማይገኝለት የሃገራችን ሰላም ተግተን እንሰራ ዘንድ እያሳሰብን በዚህ አጋጣሚ ህይወታቸውን ላጡና ያካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን በድር ኢትዮጵያ የተሰማውን መሪር ሃዘን ይገልጻል።
መንግስትም ሂደቱን ተከታትሎ ውጤቱን ለህብረተሰቡ ቢገልጽ መልካም ነው እንላለን።
አላህ ሃገራችንንም ሰላም እንዲያደርግልን እንለምነዋለን።
በድር ኢትዮጵያ ሰሜን አሜሪካ ኦክቶበር 28 2019
የሃገራችንን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ ከበድር ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ
