19 ኛዉ የበድር ጉባኤ ተጠናቀቀ­­­­­­­

 

19 ኛዉ የበድር ጉባኤ ተጠናቀቀ­­­­­­­

           በድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ላለፉት 18 ዓመታት አመታዊ ጉባኤዉን በሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ስቴቶች ሲያካሄድ ቆይቷል። የዘንድሮዉንም 19ኛዉን ጉባኤ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር በሲያትል ( ኢማስ ) አዘጋጅነት በዋሽንግተን ስቴት በቤልቬዩ ሂልተን ሆቴል ክንዉኑ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል። የኢማስ አባላትም ለፕሮግራሙ መሳካት ያሳዩት የተቀናጀ ሥራ ዉጤት ምስጋናችን የላቀ ሲሆን ለሌሎችም ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል በመተማመን ነዉ፣ 

         በጉባኤዉም በዋነኛነት ትኩረት ተሰጥቶት አንድ መስማሚያ ላይ የተደረሰዉ በድር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ብሎም በሀገራችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ድርጅት እንዲሆን ለማብቃት በጥናት ቡድኑ ተዘጋጅቶ የቀረበዉን ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንዲቻል በቀጣይ ስድስት ወራት ዉስጥ ቅድሚያ ከሚሰጣቸዉ ዋናዎቹ ስራዎች አንዱ ሲሆን ጎን ለጎን የድርጅቱን የፋይናንስ አቅም ማጎልበትና የድርጅቱን ጽ/ቤት ኢትዮጵያንም ጨምሮ ለዉጤት እንዲበቁ ማስቻል ነዉ።    

       በቀጣይ ዓመት የሚዘጋጀዉ 20ኛዉንም ጉባኤ በድር ኢትዮጵያ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚያዘጋጅ ሲሆን ይህም ድርጅቱ የተቋቋመበትን 20ኛዉን ዓመት ምክንያት በማድረግ ሰፋ ያሉ ፕሮግራሞች እንደሚጠበቁ ይታመናል፣ 

BADR ETHIOPIA JULY 4 – 7 / 2019 CONVENTION SEATTLE , WA

Leave a comment

All comments are moderated before being published