የመጅሊሱን ህልዉና ማስቀጠል

የመጅሊሱን ህልዉና ማስቀጠል 

    የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሀገራችን መብቱንና የእምነት ነጻነቱን ለማስከበር ለዘመናት ታግሏል።  በዘመናቱ ዉስጥም በወታደራዊ መንግስት ወቅት የበዓላት እና የሚወከለዉ መጅሊስ ከመመስረት ባሻገር እንደ ዜጋ የመብት መከበር ሊጎናጸፍ አልቻለም። ባለፉት 27 ዓመታትም ይህ ብቸኛዉ ብርቅዬ ድርጅቱን ከህዝበ ሙስሊሙ ለመንጠቅ ብሎም በእምነታችን ዉስጥ ጣልቃ በመግባት ከምንግዜዉም በከፋ ሁኔታ ተጽእኖዉ ቀጥሎ እንደነበር እና በተለያዩ ጊዜያትም ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማዳከም ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል።    

      የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለዘመናት ሲታገሉለት የነበረዉን የመብት ጥያቄ ከግቡ ለማድረስ በተለይ ባለፉት ሰባት ዓመት እስከ ህይወት መስዋእትነት የተክፈለበት ሰላማዊ የእምነት ነጻነት ጥያቄ ተከናዉኖ አንጻራዊ ምላሽ ማግኘት በጀመረበት በአሁኑ ወቅት ከአባታችን ተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጅ ኡመር እድሪስ መጅሊስን በማስመልከት የሰጡትን መግለጫ መላዉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ህብረተሰብ እንደተከታተለዉና ከመግለጫዉ እንደምንረዳም ተቋሙን ለማስተዳደር የተረከበዉ አዲሱ ቦርድ ተቋሙን ሲረከቡት ለአንድ ወር ለሰራተኛ የሚከፈል በጀት እንኳ በካዝና ዉስጥ አለመኖሩን ከመስማት በላይ የሚዘገንን ጉዳይ የለም።  

      ይህ ብቸኛዉ ተቋምን ማደራጀት ብሎም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ የሁላችንም ግዴታ መሆኑን አዉቀን በፍጥነት በመረባረብ ዛሬ ነገ ሳንል የቀረበዉን ጥሪ ተቀብለን የእቅማችንን ያህል የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል እንደወትሮዉ ፈጣን እንቅስቃሴ በማድረግ ለዉጤት ለማብቃት አብረን ልንቆም ስለሚገባ የመጅሊሱን ህልዉና የማስቀጠል ጥረታችንን   ለመወጣት ዝግጁነታችንን ማሳየት እንደሚገባን በድር ኢትዮጵያ አበክሮ ያሳስባል።

አላሁ አክበር !!

በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ  ግንቦት 31 2019

Leave a comment

All comments are moderated before being published