News Feed From Ethiopia.

የሃገራችንን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ ከበድር ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ

Posted by Badr Ethiopia on

የሃገራችንን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ ከበድር ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያውያ ለረዥም ዓመታት በዓለም ላይ ከምትታወቅባቸውእሴቶቿ መካከል ተቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው አንድነትን አጎልብቶልዩነትን አጥብቦ ተሳስቦ በጋራ አብሮ መኖርን ነው። ሰሞኑን የተከሰተውአሳዛኝ ሁኔታ ይህን ለዘመናት ያጋመደንን ወገን ሇወገኑ የሚለውንብሂላችንን የሚጻረር መሆኑ አያጠያይቅም።ስለዚህ ሁለም የሚያምረውበሃገር ላይ ሰላምና መረጋጋት ሲኖር ስለሆነ የአመለካከት ልዩነቶችንበዉይይት እየፈታን ሁላችንም አማራጭ ለማይገኝለት የሃገራችን ሰላምተግተን እንሰራ ዘንድ እያሳሰብን በዚህ አጋጣሚ ህይወታቸውን ላጡናያካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን በድር ኢትዮጵያ የተሰማውን መሪርሃዘን ይገልጻል። መንግስትም ሂደቱን ተከታትሎ ውጤቱን ለህብረተሰቡቢገልጽ መልካም ነው እንላሇን።      አላህ ሃገራችንንም ሰላም እንዲያደርግልን እንለምነዋለን።           በድር ኢትዮጵያ      ሰሜን አሜሪካ   ኦክቶበር 28 2019

Read more →

የአንድነት ማፅኛ ረቂቅ ሰነድ ለዉይይት ቀረበ

Posted by keder nuru on

የአንድነት ማፅኛ ረቂቅ ሰነድ ለዉይይት ቀረበ

የአንድነት ማፅኛ ረቂቅ ሰነድ ለዉይይት ቀረበ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ዛሬ በሙሀረም 1 ቀን 1440 ዓመተ ሂጅራ (መስከረም አንድ፣ 2011) በአሁኑ ሰዓት በኮሚቴው ቢሮው ዉስጥ የሙስሊሞችን ልዩነት በዘላቂ መመሪያ ወደ አንድነትና ትብብር በመለወጥ ለማጽናት በተዘጋጀው ረቂቅ ላይ የሁሉንም መዝሀቦችንና ጀመዓዎችን የሚወክሉ ዓሊሞቸ በተገኙበት ዉይይት ተደረገ። ረቂቅ ሰነዱን በዛሬው መድረክ የተጋበዙ ዓሊሞች ወደየቤታቸው በመውሰድ በ10 ቀናት ውስጥ በአስተያየታቸው ካዳበሩት በዃላ የተሻሻለው ሁለተኛው ረቂቅ በቅርቡ ለህዝቡና በየክልሉ ያሉ ዑለሞች ጭምር ቀርቦላቸው ሀሳቦቻቸውን ካከሉበት በዃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ሰነዱ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ሲደርስ በዋናው ኮሚቴው የተዋቀሩት እና እየሰሩ ያሉት ሁለቱ ተጨማሪ ንዑስ ኮሚቴዎች ማለትም የመጅሊስ አወቃቀር ላይ እየሰራ ያለው ኮሚቴ(በአህመዲን ጀበል...

Read more →

በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አስተባባሪነት የተዘጋጀ የኡለማዎች የስምምነት ሰነድ

Posted by keder nuru on

በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አስተባባሪነት የተዘጋጀ የኡለማዎች የስምምነት ሰነድ

በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አስተባባሪነት የተዘጋጀ የኡለማዎች የስምምነት ሰነድ (ለተጨማሪ ውይይት የቀረበ) ******************************ክፍል ሁለት(የቀጠለ)I. ለሊቃውንቱ (ለዓሊሞች) ስምምነት የቀረቡ ነጥቦች፣ 1. የእስልምና የኢማን (ተውሂድና አቂዳ) ምንጮችና መሠረቶች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ ቁርኣን፣ ሀዲስ (ሱና) እና ኢጅማዕ መሆናቸውን እናፀናለን፤ 2. የእስልምና ሕግጋት (አህካም) ዋነኛ ምንጮችና መሠረቶች እንደ ቅደም ተከተላቸዉ ቁርኣን፣ ሀዲስ (ሱና)፣ኢጅማዕ እና ቂያስ መሆናቸውን እናፀናለን፤ 3. የነቢዩን ሶሀባዎች፣ የአማኞችን እናቶች እንወዳለን፡፡ ከነርሱ በኋላ የመጡና እነርሱን በቅንነት የተከተሉ ሙእሚኖችን (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) ማለትም ታላላቅ መሪዎችን፣የዲናችንን ፉቀሀዎች ከመጀመሪያው ትውልድም ሆነ ከእነርሱ በኋላ የመጡትን በኪታብና ሱንና የጸኑትን የአህለ ሱንና ወል ጀማዓ ትውልዶችን ማለትም የሀዲስ አዋቂዎችን (ኡለማኡል ሀዲስ ወል አሰር)፣ የፊቂህና የተውሂድ ጽንሰ ሀሳብ (ነዞር) ዑለማዎችን፣...

Read more →

ጠ/ሚር ዐቢይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር ታሕሳስ 4, 2011 ተወያዩ።

Posted by keder nuru on

ጠ/ሚር ዐቢይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር ታሕሳስ 4, 2011 ተወያዩ።

ጠ/ሚር ዐቢይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር ታሕሳስ 4, 2011 ተወያዩ። ውይይቱም በዋናነት የኮሚቴውን የ5 ወራት የግጭት አፈታት እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን የተመዘገበውን ለውጥ በተለይም በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የጋራ የሆነ አንድነትን የሚያጠናክር ተቋም መመስረቱን መንግስታቸው እንደሚያደንቅ ገልፀዋል። በተጨማሪም ጠ/ሚሩ የታዩትን መግባባቶችን ለማጠናከርና እነሱንም ለማደናቀፍ የሚሰሩ ማናቸውንም እንቅፋቶች ለመከላከል የመንግስታቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

Read more →

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ታህሳስ 3/2011 ከሰላም ሚኒስትሯ ከወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በሚኒስቴር መሥርያቤቱ ዉይይት አድርጓል።

Posted by keder nuru on

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ታህሳስ 3/2011 ከሰላም ሚኒስትሯ ከወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በሚኒስቴር መሥርያቤቱ ዉይይት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ታህሳስ 3/2011 ከሰላም ሚኒስትሯ ከወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በሚኒስቴር መሥርያቤቱ ዉይይት አድርጓል። በዉይይቱ የኮሚቴው አባላት የእስካሁኑን የሥራ ሂደታቸውንበመግለፅ የገጠሟቸውን ተግዳሮቶችን አብራርተዋል። ሚኒስትሯም ከመጅሊስ መዋቅርም ሆነ ከዉጭ የኮሚቴውን ተግባራት ሊያደናቅፉ ስለሚጥሩ አካላት እና መስሥሪያቤታቸውም የህዝቡን አንድነትና ሰላም የሚያደፈርሱትን እንደማይታገስ ገልፇል:: ሚኒስትሯ የኮሚቴው አባላት በአንድነት የህዝቡን ፍላጎት ለማርካት የሚያደርጉትን ጥረትና መናበብ እንዳስደሰታቸው ገልፀው መንግስት አንድነቱን የጠበቀ ሙስሊም ህብረተሰብ እንደሚፈልግ አብራርተዋል። የተከፋፈለ ሙስሊም ህብረተሰብ ለራሱ ለሙስሊሙና ለሀገሪቷም እንደማይፈይድ አብራርተዋል። ሚንስትሯ በተጨማሪም የኮሚቴውን የእስካሁኑ የሥራ ሂደት አድንቀው የኮሚቴውን ተግባራት የሚያደናቅፍን የትኛውንም አካል በዝምታ እንደማይመለከት ገልፇል:: እንዲሁም የህዝቡን ፍላጎት ለማርካት እና ሰላምን ለማስፈን ሲባል ከኮሚቴው ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልፇል::...

Read more →