የአንድነት ማፅኛ ረቂቅ ሰነድ ለዉይይት ቀረበ

የአንድነት ማፅኛ ረቂቅ ሰነድ ለዉይይት ቀረበ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ዛሬ በሙሀረም 1 ቀን 1440 ዓመተ ሂጅራ (መስከረም አንድ፣ 2011) በአሁኑ ሰዓት በኮሚቴው ቢሮው ዉስጥ የሙስሊሞችን ልዩነት በዘላቂ መመሪያ ወደ አንድነትና ትብብር በመለወጥ ለማጽናት በተዘጋጀው ረቂቅ ላይ የሁሉንም መዝሀቦችንና ጀመዓዎችን የሚወክሉ ዓሊሞቸ በተገኙበት ዉይይት ተደረገ። ረቂቅ ሰነዱን በዛሬው መድረክ የተጋበዙ ዓሊሞች ወደየቤታቸው በመውሰድ በ10 ቀናት ውስጥ በአስተያየታቸው ካዳበሩት በዃላ የተሻሻለው ሁለተኛው ረቂቅ በቅርቡ ለህዝቡና በየክልሉ ያሉ ዑለሞች ጭምር ቀርቦላቸው ሀሳቦቻቸውን ካከሉበት በዃላ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ሰነዱ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ሲደርስ በዋናው ኮሚቴው የተዋቀሩት እና እየሰሩ ያሉት ሁለቱ ተጨማሪ ንዑስ ኮሚቴዎች ማለትም የመጅሊስ አወቃቀር ላይ እየሰራ ያለው ኮሚቴ(በአህመዲን ጀበል የሚመራ የ14 የባለሞያዎች ስብስብ) እና በዶ/ር መሀመድ ሀቢብ የሚመራ የህግ ባለሞያዎች ኮሚቴ የደረሱበትን ረቂቅ ባንድነት በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ ተደርጎ የሚመለከታቸው አካላት በተለያዩ መንገዶች አስተያየታቸውን በመስጠት ካሻሻሉት በኋላ ፀድቆ ወደ ተግባር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። የአንድነት ሰነዱ በሁሉም ወገኖች ስምምነት ከፀደቀ በዃላ ወደፊት ከሁሉም ወገኖች የሚቋቋመው የዑለማ ምክር ቤትና መጅሊስ የሙስሊሞችን አንድነት ጠብቆ የሚጓዝበት ገዢ መመሪያ ይሆናል።

Leave a comment

All comments are moderated before being published