የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ታህሳስ 3/2011 ከሰላም ሚኒስትሯ ከወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በሚኒስቴር መሥርያቤቱ ዉይይት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ታህሳስ 3/2011 ከሰላም ሚኒስትሯ ከወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በሚኒስቴር መሥርያቤቱ ዉይይት አድርጓል። 
በዉይይቱ የኮሚቴው አባላት የእስካሁኑን የሥራ ሂደታቸውንበመግለፅ የገጠሟቸውን ተግዳሮቶችን አብራርተዋል። 
ሚኒስትሯም ከመጅሊስ መዋቅርም ሆነ ከዉጭ የኮሚቴውን ተግባራት ሊያደናቅፉ ስለሚጥሩ አካላት እና መስሥሪያቤታቸውም የህዝቡን አንድነትና ሰላም የሚያደፈርሱትን እንደማይታገስ ገልፇል::

ሚኒስትሯ የኮሚቴው አባላት በአንድነት የህዝቡን ፍላጎት ለማርካት የሚያደርጉትን ጥረትና መናበብ እንዳስደሰታቸው ገልፀው መንግስት አንድነቱን የጠበቀ ሙስሊም ህብረተሰብ እንደሚፈልግ አብራርተዋል። የተከፋፈለ ሙስሊም ህብረተሰብ ለራሱ ለሙስሊሙና ለሀገሪቷም እንደማይፈይድ አብራርተዋል።

ሚንስትሯ በተጨማሪም የኮሚቴውን የእስካሁኑ የሥራ ሂደት አድንቀው የኮሚቴውን ተግባራት የሚያደናቅፍን የትኛውንም አካል በዝምታ እንደማይመለከት ገልፇል:: እንዲሁም የህዝቡን ፍላጎት ለማርካት እና ሰላምን ለማስፈን ሲባል ከኮሚቴው ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልፇል::

የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ በሃይማኖት ምክንያት ግጭት ሊፈጥሩ ስለሚፈልጉ አካላት መንግስት በቂ መረጃ እንዳለው ገልፀው ከአሁን በዃላ በዝምታ እንደማይታለፍ ገልፀዋል።

Leave a comment

All comments are moderated before being published