News feed From Diaspora

የበድር ኢትዮጵያ የጉባኤ የአቋም መግለጫ

Posted by keder nuru on

የበድር ኢትዮጵያ የጉባኤ የአቋም መግለጫ

በድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በ2018 በሰላም ፋዉንዴሽን ኮምዩኒቲ አዘጋጅነት ከጁላይ 26 እስከ 29 በተካሄደዉ 18 ኛዉ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶክተር አቢይ አህመድ ፤ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር የክቡር ዶክትሬት አቶ ለማ መገርሳ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኢንጂነር በድሩ ሁሴን ሌሎችም ዉድና የተከበሩ ኡስታዞቻችን በተሳተፉበት በዚሁ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ የተሰጡ ትምህርቶች እና የተላለፉ የመፍትሄ ሀሳቦችን ግምት ዉስጥ በማስገባት በጉባኤዉ ማጠቃለያ የሚከተለዉን ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በጋራ አዉጥተናል። 1. ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አቢይ አህመድ አሊ እና አመራራቸዉ በሚተገብሩት ፈጣን የለዉጥ ሂደት ሀገራችን ወደ ተሻለ...

Read more →

የጋራ አቋም መግለጫ

Posted by keder nuru on

የጋራ አቋም መግለጫ

የጋራ አቋም መግለጫ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉእንደሚታወቀው በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዘርፈ ብዙ የሆነውን የማህበረሰባችንን ሃይማኖታዊ እና ማህበራዊ ፍላጎቶች ለማሟላት ተደራጅተን ስንንቀሳቀስ ቆይተናል፡፡ በመካከላችን ማጎልበት የምንፈልገውን መንፈሳዊ ትስስር በሚያሳድጉ ስራዎች ላይ ከማተኮራችን በተጨማሪ በሀገርቤት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሚመለከቱ እና አጠቃላይ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የድርሻችንን ለመወጣት ስንጥር ቆይተናል፡፡ እነዚህን የመሰሉ ክንዋኔዎችን በተደራጀ መልኩ ለመስራት በምናደርገው ጥረት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደቻልነው ሁሉ በረጅም ዓመታት ጉዟችን ውስጥ የአካሄድ ልዩነቶች እየተፈጠሩ ሂደታችን ሲገታ እና በመካከላችን ቅራኔዎች ሲፈጠሩ መቆየታቸውም አልቀረም፡፡ እነዚህን ክፍተቶች በግዜ ለማጥበብ የተደረጉ የውስጥ ጥረቶች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ባለመቻላቸው በማህበረሰባችን ጉዳይ ላይ ልናበረክት የምንችለውን አስተዋፅኦ ከማስተጓጎሉ...

Read more →

“ትውልድን በጋራ እንታደግ”

Posted by keder nuru on

“ትውልድን በጋራ እንታደግ”

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ። “ትውልድን በጋራ እንታደግ” በሚል መሪ ቃል ከ July 4 እስከ July 7 በታሪካዊቷ የሲያትል ከተማ በኢማስ ኮሚኒቲ አዘጋጅነት በቤልቪው ሂልተን ሆቴል በሚዘጋጀው 19ነኛው የበድር ኮንቬንሺን ላይ ሁላችሁም እንድትገኙ በድር ኢትዮጲያ ሲጋብዝዎ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል።ባለፈው አመት ብዙ ታሪካዊ ክስተቶችን ያስመዘገበው አንጋፋው ድርጅት በድር ኢትዮጲያ በዚህም ኮንቬንሺን ኑ አብረን ታሪክ እንስራ ይሎታል። በድር ኢትዮጲያ

Read more →