Official Announcements From Badr

ለክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ

Posted by Badr Ethiopia on

ለክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋ

   በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ ከበድር ኢትዮጵያለክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋለኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲዋሽንግተን ዲሲ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉንም ባስደነቀ የለዉጥ ሂደት ላይ እንደምትገኝ ግልጽ ነዉ። ይህ ለዉጥ እዉን እንዲሆን በርካታ ሀገራችን ህዝቦች ዉድ ዋጋ ብሎም ብዙ መስዋእትነት የከፈሉለት መሆኑም ሊዘነጋ የሚችል አይደለም። እንደሚታወቀዉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ለሰብአዊ መብታቸዉ እና ለእምነት ነጻነታቸዉ መከበር በግንባር ቀደምትነት በመቆም በሰላማዊ ትግል መርህ መሰረት ለመብት መከበር በአንድነት እና በጽናት እንዴት መቆም እንደሚቻል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማድረግ በመቻላቸዉ ድንቅ ምሳሌ ለመሆን በቅተዋል ።ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በሁሉም መስክ የለዉጡ አካልና አጋዥ በመሆን እንደ ዜጋ የሚጠበቅበትን ሁሉ በማድረግ የዜግነት ግዴታዉን እየተወጣ ይገኛል። ሀገራችንን...

Read more →

አስደሳች ዜና ከወደ ሲያትል

Posted by keder nuru on

አስደሳች ዜና ከወደ ሲያትል

Al-Imran (103) … وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا“And hold fast, all of you together, to the rope of Allah (i.e. Qur’an), and benot divided among yourselves…’’በሀገራችን በተለይ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ይደርስ በነበረዉ ዘመን ተሻጋሪ አስከፊ ችግሮች ሳቢያ የነበሩ ብሶቶችን አግባብባለዉ መልኩ ለመንግስት በማቅረብ ዘላቂ ምላሽ እንዲያገኙ በሚል የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ድምጻችን ይሰማበሚል መርህ ቃል ታጅቦ በሰላማዊ መንገድ የእምነት ነጻነቱን ለማስከበር እንቅስቃሴ ሲጀመር በሰሜን አሜሪካ የሚገኙኮምዩኒቲዎች እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ተንቀሳቅሰዋል ።በዚያ ወሳኝ ሂደት የጉዳዩ ግዙፍነት፤ አጣዳፊነት እና ወቅታዊነት የተነሳ ይደረጉ የነበሩ ርብርቦሾች የታሰበዉን ለዉጥ በሚፈለገዉመልኩ ለማምጣት ባለመቻላቸዉና በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን እንዲሁም ከነሱ ጋር ተያዣዥነት ባለዉ...

Read more →

በመስጂዶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቀን እንቃወማለን

Posted by keder nuru on

በመስጂዶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቀን እንቃወማለን

በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ከተማ በቀበሌ 03 በጥር 26/2011 ዓ.ል ሁለት መስጂዶችን ሙሉበሙሉ ያወደመና በሌላ አንድ መድጂድ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ወንጀል ተፈጽሟል ። በተጨማሪ በሙስሊም   በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ ወገኖቻችን ላይ ድብደባና በንግድ ቤቶቹ ላይ ጉዳት ተከስቷል።በድር ኢትዮጵያ ይህንን ድርጊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በጽኑ ያወግዛል። ለዚህ ድርጊት የሚያበቃ ምንም አይነትምክንያትም ተቀባይነት የለዉም ብሎም ያምናል። የችግሩ መነሻ የተባለዉና በሰርግ ፕሮግራም ላይ ተገኘ ስለተባለዉምስልም በሰዓቱ በነበሩ የአካባቢዉ ሰዎችና ያገር ሽማግሌዎች ምክክር ተደርጎበትና ሰላም ወርዶ ሳለ ሁኔታዉንከማብረድ ይልቅ አባብሶ በመስጂዶች ላይ በመዝመት በእሳት ማጋየት ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የማይጠበቅ ከመሆኑምበላይ አገራችን በጀመረችዉ የለዉጥ ጎዳና ላይ ሳንክ እንዳይሆን...

Read more →

የበድር ኢትዮጵያ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

Posted by keder nuru on

የበድር ኢትዮጵያ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉየበድር ኢትዮጵያ ጉባኤ የአቋም መግለጫበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በ2018 በሰላም ፋዉንዴሽን ኮምዩኒቲ አዘጋጅነት ከጁላይ 26 እስከ 29በተካሄደዉ 18 ኛዉ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶክተር አቢይ አህመድ ፤ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድርየክቡር ዶክትሬት አቶ ለማ መገርሳ እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኢንጂነር በድሩ ሁሴን ሌሎችም ዉድና የተከበሩ ኡስታዞቻችን በተሳተፉበት በዚሁታሪካዊ ጉባኤ ላይ የተሰጡ ትምህርቶች እና የተላለፉ የመፍትሄ ሀሳቦችን ግምት ዉስጥ በማስገባት በጉባኤዉ ማጠቃለያየሚከተለዉን ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በጋራ አዉጥተናል።1. ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አቢይ አህመድ አሊ እና አመራራቸዉ በሚተገብሩት ፈጣን...

Read more →