የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለማችን

   የኮሮና ቫይረስ Coronavirus disease (COVID-19) በ2019 በቻይና ዉሀን በሚባል ግዛት መነሾነት የተከሰተዉ በአሁኑ ወቅት ዓለምን አንጣሎ እያናወጠዉ እንደሚገኝ በሰፊዉ እየተዘገቡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቻይናን ባስጨነቀበት ወቅት ትኩረት ያልሰጡ ሀገራትም በአሁኑ ሰዓት ከመራወጣቸዉ ባሻገር እንደ ጣሊያን ያሉ ሀገራት ደግሞ የሟቾች ቁጥር በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከቻይና በልጦ መገኘቱ  ዓለምን እያሸበረ ይገኛል።

    እስከአሁን ምንም አይነት በዉል የሚታወቅ መፈወሻ መድሀኒት ያልተገኘለት ይኸዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ሕዝብ ላይ ፈተናን በደቀነበት በዚህ ወቅት በቫይረሱ የሚያዙና የሟቾች ቁጥር እድገቱ እየጨመረ ይገኛል። በበሽታዉ ይበልጥ ተጠቂ የሆኑ ከተሞች እና ሀገራትም ህዝቦቻቸዉ ከእንቅስቃሴዎች ሁሉ ታግደዉ በየቤታቸዉ እንዲቆዩ ብሎም መደበኛ ስራዎቻቸዉን ሁሉ በየቤታቸዉ ሆነዉ እንዲሰሩ የተደረገበት ወቅት ላይ ተደርሷል።በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ ምን ሊከተል እንደሚችል መገመት አይከብድም።

   የኢትዮጵያዉያን ማህበረሰብም በአብዛኛዉ ስራዎቻችን አገልግሎት ከመስጠት ጋር የተቆራኘ እንደ መሆኑ መጠን በበሽታዉ የመጋለጥ ደረጃዉ የሰፋ ስለሚሆን እጅጉን አሳሳቢ ነዉና በተቻለን መጠን ለጥንቃቄ በሚል የሚነገሩትን ሁሉ ለሟሟላት ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅብን ሁሉ ኮምዩኒቲዎችም ከመቼዉም በበለጠ ትኩረት ለማህበረሰባችን አገልግሎት መስጠት ላይ የሚገባን ወቅት በመሆኑ ጊዜያዊ ኮሚቴ በማዋቀር ህዛባችንን በቀጥታ መርዳት በሚገቡን ጉዳዮች ሁሉ ፈጥነን ለመድረስ እንዲቻል አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት እንድናደርግ አበክረን ለማሳሰብ እየወደድን በሌላ መልኩ አብዛኛዉ ማህበረሰባችንም እቤት ዉስጥ የሚገኝ በመሆኑ አስፈላጊ መረጃዎች እና የዲን ትምህርቶችን በቀጥታ ስርጭት ለማድረስ በሚቻልበት መልኩ በድር ኢትዮጵያ የሙስሊሞች ድርጅት ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቸን ስለሆነ እንድትከታተሉን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን።

    የበሽታዉ የመስፋፋት ሂደት ሲታይ ሌላዉ እጅጉን የሚያሳስበዉ ጉዳይ በሀገራችን ኢትዮጵያ የህዝቡ አኗኗር እና ቁርኝቱ እጅግ በጣም የተቀራረበ ከመሆኑ አንጻር እንዲሁም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ፤ የባለሙያ እና የተቋማት ደረጃ ሲታይ ሀገሪቷ ልትወጣዉ ከማትችልበት አዘቅት ዉስጥ ሊከታት የሚችል ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተነዉ ባገኘነዉ አጋጣሚ ሁሉ ለህዝቡ የበሽታዉ አስከፊነት እና ወረረሽኝነቱን በመረዳት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚገባን ሆኖ የከፋ ነገር ከመጣ ከዚህ ቀደም እንደምናደርገዉ ሁሉ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እንድናደርግ በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን። አላህ (ሱወ) ከፈተናዉ ይጠብቀን

“ O ALLAH! I SEEK REFUGE IN YOU FROM LEPROSY, INSTANTY, ELEPHANTIASIS, AND EVIL DISEASES.’’

በድር ኢትዮጵያ   ሰሜን በአሜሪካ   ማርች 22 2020                           

Leave a comment

All comments are moderated before being published