ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በጋራ እንተባበር

  የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ በዓለማችን ከፍተኛ ሀብት ፤ ኢኮኖሚ፤ የተደራጀ የህክምና ተቋማት እና በቂ የሰለጠነ የሰዉ ኋይል አላቸዉ የሚባሉ ታላላቅ ሀገራት ሁሉ ሊቋቋሙት ያልቻሉት በፈጣን ወረርሽኝነት   ኮሮና ቫይረስ 19 በመባል የሚታወቀዉ ወረርሽ በርካታ የህዝብ ቁጥር ህይወትን እየቀጠፈ ይገኛል።

  ይህ አስከፊ በሽታ በሀገራችን በአሁኑ ወቅት ምንም እንኳን ትንሽ ቁጥር ያለዉ ቢሆንም የማህበረሰባችን የአኗኗር ፤ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ሲታይ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በማሻቀብ በማህበረሰቡም ሆነ በመንግስት ደረጃ ሊቋቋሙት ከሚችሉት በላይ እንደሚሆን ከፍተኛ ግምት እንዳለና ቀደም ሲልም ባወጣነዉ የአቋም መግለጫ ላይ የኛ ድጋፍ ሊቀጥል እንደሚገባ መግለጻችን ይታወቃል። ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ብሎም ከማህበረሰቡ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ከግምት ዉስጥ በማስገባት በድር ኢትዮጵያ ባዋቀረዉ ግብረሀይል አማካይነት ዓለም አቀፍ የገንዘብ አሰባሰብ መርሀ ግብር መነደፍ እንዳለበት      ዉሳኔ ላይ በመደረሱ በሀገራችን ለሚከሰተዉ ወረርሽ ለመከላከል እንዲቻል ሀገራዊ እንቅስቃሴ   ለማድረግ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥሪ አዘጋጅቷል።        

   የወቅቱ ሁኔታም በየኮምዩኒቲያችን ተሰባስበን ማድረግ የማንችልበት ሂደት ላይ ስለምንገኝ ጎፈንድሚ አካዉንት (ኦንላይን) የገንዘብ አሰባሰብ ተመቻችቷል። ከዚህ ቀደም ካደረግናቸዉ ማናቸዉም አይነት የገንዘብ አሰባሰብ በተሻለ ደረጃ ለዉጤት እንድናበቃዉ ኢትዮጵያዉያንን በክብር እየጠየቅን አላህ (ሱወ) ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ህዝቡን እንዲጠብቀዉ ብሎም የዘንድሮን ረመዳን በመስጂዳችን ተገናኝተን ለመጾም ያብቃን በማለት ፈጣሪያችንን እየተማጸን ሊንኩን በመጫን ድጋፎን ይለግሱ።

ሊንኩን ይጫኑ   https://charity.gofundme.com/o/en/campaign/help-ethiopian-fight-corona       

በድር ኢትዮጵያ          ሰሜን አሜሪካ         አፕሪል 3 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published