እንኳን ለ1441ኛዉ የረመዳን ወር አደረሳችሁ

  በድር ኢትዮጵያ እንኳን ለ 1441 ኛዉ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን እያለ የዘንድሮዉ ረመዳን በኮረና ቫይረስ (COVID-19) ምክንያት በረመዳን የተለመደዉን የጀምዓ ኢፍጣርና ሰደቃ የሚደረግበት ባለመሆኑ ብዙ ሙስሊም ቤተሰቦችና አካለ ደካሞች በላቀ ችግር ላይ እንደሚሆኑ ግልጽ ነዉ።

   ስለሆነም በዚህ የሰደቃና የልግስና ወር የበለጠ ተጠቃሚ እንድንሆን ችግርተኞችን ፤ አቅመ ደካሞችንና ጠዋሪ ያጡትን በየቤታቸዉ እርዳታ እንዲደርሳቸዉ በማድረግ የወርሃ ረመዳን አጅር (ትሩፋት) አፋሽ እንድንሆን ፤ ሁሉም በየአካባቢዉ የእርዳታ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።

   እንዲሁም በኮቪድ 19 ምክንያት ችግር ላይ ላሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት በድር ኢትዮጵያ ለሚያደርገዉ ጥረት በጎፈንድሚም ሆነ በየኮምዩኒቲዎቻችን በተዘጋጁ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች በመሳተፍ የድርሻችንን እንድንወጣ እናሳስባለን። ይህንንም ወረርሽን (ኮቪድ19) አላህ (ሱ.ወ) ያስወግድልን። 

በድር ኢትዮጵያ   ሰሜን አሜሪካ  April 22, 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published