አወልያን ለማቋቋም እንዘጋጅ

አወልያን ለማቋቋም እንዘጋጅ

    በሀገራችን ኢትዮጵያ የሙስሊሙን ማህበረሰብ እገዛና ድጋፍን የሚሹ በርካታ ተግባራቶች ከፊት ለፊታችን ቆመዉ እንደሚጠብቁን ግልጽ ነዉ። ለዚህም ዋነኛዉ ምክንያት ለዘመናት ሙስሊሙን ማህበረሰብ አንቀሳቅሶ በየጊዜያቱ ሰብዓዊ መብቶችንና መሰል ሂደቶችን የሚያስፈጽም ሁነኛ አካል አለመኖሩም ነበር።

    በአወልያ በ2004 የተቀጣጠለዉ ህዝባዊ አመጽ ሀገራዊ ለዉጡን አስከትሎ ለድል ሲበቃ ሌሎችንም በርካታ መሰረታዊ ለዉጦችንም አያያዞ አስመዝግቧል። የትግሉ ፈር ቀዳጅ ፤ የአሻራችን ጥንስስ የተጣለበት አወልያ አሁን ደግሞ የእኛን ድጋፍ ይፈልጋል። የዚሁ ባለዉለታ ተቋማችን ያለበትን አደረጃጀት ለማሻሻል ብሎም ዘላቂነት ባለዉ መልኩ ለማቋቋም እንዲቻል በሀገር ቤት እና ከሀገር ቤት ዉጭ ግብረ ሃይል ተዋቅሮ በቅድሚያ ለትዉልድ ታሪክና ዘመን ተሻጋሪ በሆነዉ ስራ ’’ ሆስፒታሉን እናስጨርስ’’ በሚል መርህ የገንዘብ አሰባሰብ ስራዎች በሰፊዉ ተጀምረዋል። በወቅቱ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ለመቃወም በተደረገዉ እንቅስቃሴ በጋራ ቆመን እንዳሳየነዉ ሁሉ አሁንም ለግንባታ ፕሮጀክቱ ተግባራዊነት ለቀረበዉ ጥያቄ የገንዘብ እርዳታም ከጎናቸዉ መቆም ይጠበቅብናል።

   ይህንኑ ሥራ ለዉጤት ለማብቃትና የኛንም አሻራ ለማሳረፍ እንድንችል በቅርቡ በበድር ኮምዩኒቲዎች አማካይነት የገንዘብ ማሰባሰብ ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች በመመቻቸት ላይ ናቸዉና ስራዉን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል በሚቻልበት መልኩ እስኪጀመር ድረስ በቂ ግንዛቤ ኖሮን የተጣለብንን ህዝባዊ ሀላፊነት ለመወጣት በዝግጅት እንጠባበቅ እንላለን።  

አላሁ አክበር

በድር ኢትዮጵያ     ሰሜን አሜሪካ    ሜይ 24 2020                       

Leave a comment

All comments are moderated before being published