በመስጂዶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቀን እንቃወማለን

በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ከተማ በቀበሌ 03 በጥር 26/2011 ዓ.ል ሁለት መስጂዶችን ሙሉ
በሙሉ ያወደመና በሌላ አንድ መድጂድ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ወንጀል ተፈጽሟል ። በተጨማሪ በሙስሊም

 

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

ወገኖቻችን ላይ ድብደባና በንግድ ቤቶቹ ላይ ጉዳት ተከስቷል።
በድር ኢትዮጵያ ይህንን ድርጊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በጽኑ ያወግዛል። ለዚህ ድርጊት የሚያበቃ ምንም አይነት
ምክንያትም ተቀባይነት የለዉም ብሎም ያምናል። የችግሩ መነሻ የተባለዉና በሰርግ ፕሮግራም ላይ ተገኘ ስለተባለዉ
ምስልም በሰዓቱ በነበሩ የአካባቢዉ ሰዎችና ያገር ሽማግሌዎች ምክክር ተደርጎበትና ሰላም ወርዶ ሳለ ሁኔታዉን
ከማብረድ ይልቅ አባብሶ በመስጂዶች ላይ በመዝመት በእሳት ማጋየት ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት የማይጠበቅ ከመሆኑም
በላይ አገራችን በጀመረችዉ የለዉጥ ጎዳና ላይ ሳንክ እንዳይሆን ያሰጋናል ።
መንግስት ይህንን አሳፋሪ ተግባር የፈጸሙና ያነሳሱ ሀይሎችን ማንነት ላይቶ ባፋጣኝ ለፍርድ እንዲያቀርባቸዉ አበክረን
እንጠይቃለን።በዚሁ አጋጣሚ መታወቅ ያለበት በኢስላም በአስተምህሮ መሰረት ታላቅ ቦታና ክብር ከተሰጣቸዉ
እንስቶች መካከል አንዷ መርየም (ማሪያም) መሆኗ እና በቅዱስ ቁርአን ዉስጥም በስሟ የተሰየመ ምእራፍ ሁሉ
መኖሩ ኢስላም ለመርየም ያለዉን ክፍተኛ ክብር የሚያሳይ ሆኖ ሳለ ያለአግባብ ምክንያት እየተፈለገ ሙስሊሙን
ማህበረሰብ መተናኮልም ሆነ መፈታተኑን አጥብቀን እንቃወማለን።
አላሁ አክበር !

በድር ኢትዮጵያ ሰሜን አሜሪካ ፌብሩዋሪ 6 2019

Leave a comment

All comments are moderated before being published