ሼኽ ዶ/ር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ወደ አኼራ ሄዱ

የዘመናችን ታላቁ ዓሊም ሼኽ ዶ/ር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ወደ አኼራ ሄዱ

الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّـهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ ﴿البقرة

እነዚያን መከራ፤በነካቻቸዉ ጊዜ “እኛ ላአላህ ፤ ነን እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን የሚሉትን (አብስር )።   

    ለሀያ ዓመታት በመካ በኡመል ቁራ ዩኒቨርሲቲ በፕሮፌሰርነት ያገለገሉት ዓለም አቀፍ እዉቅና ያተረፉት ታላቁ ዓሊም ዶክተር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ባደረባቸዉ ህመም በመካ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ በጁን 18 2020 ወደ አኼራ ሄደዋል።     

إن الله لا يقبض العلم انتزاعاً ينتزعه من العباد، ولكن يقبض العلم بقبض العلماء، حتى إذا لم يبق عالماً اتخذ الناس رؤوساً جهالاً، فسئلوا فأفتوا بغير علم فضلوا وأضلوا

  አላህ እዉቀትን ከህዝቦቹ አይወስድም፤ ዓሊሞቻችዉን ቢወስድባቸዉ እንጂ ዓሊሞች ሲጠፉ ህዝቦች ጃሂል ወደ ሆኑ መሪዎቻቸዉ ሄደዉ ጥያቄ ይጠይቃሉ። የተሳሳተ መልስ ይሰጧቸዉና ተሳስተዉ ያሳስቷቸዋል ። ‘ኢማም ቡኻሪ’

    ዶ/ር አብዱልሽኩር ቢን መሃመድ አማን አል አሩሲ ሀረም ላይ ፈትዋ እንዲሰጡ ከተፈቀደላቸዉ በጣት  ከሚቆጠሩ የዉጭ ሀገር ዓሊሞች አንዱም ነበሩ። ዶክተር አብዱልሽኩር ከሼህ አብዱልአዚዝ ቢንባዝ ረሂመ ሁላህ  ጋር በነበራቸዉ ቀረቤታ የተነሳ ለኢልም ወደ ሳኡዲ አረቢያ የሚሄዱ ወገኖች ነጻ የትምህርት እድልና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ ያስቻሉ አባት ነበሩ። ዛሬ በሃገራችን የዲን እዉቀትን እያስፋፉ ያሉ ምሁራን የሳቸዉ ጥረት ዉጤቶች እንደሆኑም ይነገራል ። 

   በድር ኢትዮጵያ በኚህ ታላቅ ዓሊም ህልፈተ ዜና ምክንያት የተሰማዉን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ነፍሳቸዉን በጀነተል ፊርደዉስ እንዲያሳርፋት እየለመን ለቤተሰቦቻቸዉና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን ። 

በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ     ጁን 20 2020

    

 

Leave a comment

All comments are moderated before being published