ምስጋና ይገባቸዋል !!!

ምስጋና ይገባቸዋል !!!

     ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዜጎችዋ ደሀዉ ማህበረሰብ በነፍሰ ወከፍ ከተዋጣ ገንዘብ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ስታስገነባ የቆየዉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለዉጤት ለማብቃት ደፋ ቀና በሚባልበት በዚህ ፈታኝና ወሳኝ ወቅት በተለይ ከግብጽ በኩል ሰፊ የፖለቲካ ሽፋን ባለዉ መልኩ በህዳሴ ግድቡ ላይ የከፈተችዉ መጠነ ሰፊ የማደናቀፊያ ዘመቻዋ እጅግ መረን በለቀቀ መልኩ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሂደትዋ ወደፊት ይበልጥ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል አለመገንዘብዋ ነዉ።

   ዘመቻዉ በተለይ በአረብ አገሮች በአረብኛ ቋንቋ ከፍተኛ ሽፋን ያለዉ ዘገባ ሌት ተቀን እንደምታካሄድ ከዜና ምንጮች ለመረዳት ይቻላል። ይህንን የግብጾችን ድብቅ አጀንዳም እየተከታተሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በተለያዩ ታዋቂ የዜና ሚዲያዎች እና ሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም በቂ ምላሽ ከመስጠት አልፎ ለማህበረሰባችን ግንዛቤ ብሎም ለዓለም እዉነታዉን በማሳወቅ ደረጃ ከፍተኛዉን ሚና የሚጫወቱ እንደ መሀመድ አል አሩሲ ፤ ኡስታዝ ጀማል በሽር ፤ ኡመር አሊሚራህ ፤ መሀመድ ጣሀ ተወከል ፤ ኡመር ረዲ ፤ እሀታችን ዩስራ ሲራጅ ፤ወጣት ኑር ጣሂር ፤ ዉድ ኡስታዞቻችን እንዲሁም ሌሎች አጋር ተዋናዮች እንደ ሀገር ዜጋ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ኩራት ናቸዉና ልናመሰግናቸዉ ብሎም ከጎናቸዉ በጋራ በመቆም  ልንደግፋቸዉ ይገባል። 

   በድር ኢትዮጵያ የህዳሴዉን ግድብ ከሚታሰበዉ ኢኮኖሚያዊ አንጻር ብቻ ሳይሆን ከሀገር ሉአላዊነት ተለይቶ ሊታይ እንደማይገባ በጽኑ ያምናል። በራስ አነሳሽነት በሀገር ግንባታ ላይ መስዋዕትነት ከመክፈል የበለጠ አመርቂ ሀገራዊ ጉዳይ የለምና የላቀ ምስጋና እያቀረብን ሌሎችም የነሱን ፈለግ በመከተል አቅማችን በፈቀደዉ ሁሉ በሀገራችን በርካታ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባን አሳይተዉናልና እኛም ልንከተላቸዉ ይገባል በማለት በድጋሚ ይህን መሰል ፈታኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የላቀ ተሳትፎ ለምታደርጉ ጀግኖች ሁሉ ፈጣሪ ይርዳችሁ እያልን ፍትህን አንግበን የተነሳን በመሆኑ በአጭር ጊዜ ለዉጤት አንደምንበቃም በመተማመን ነዉ ። 

አላሁ አክበር

በድር ኢትዮጵያ      ሰሜን አሜሪካ      ጁን 24 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published