ለሞጣ መዋጮ ከበድር ኮምዩኒቲዎች የተሰበሰበ

     በቅርቡ በአማራ ክልል በሞጣ ከተማ በእስላም ጠል ጽንፈኞች አማካይነት በመስጂዶች እና በተመረጡ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የንግድ ተቋማት ላይ በተፈጸመዉ የእሳት ቃጠሎ ለወደሙ ንብረቶች የክልሉ መንግስት እንደተጠያቂነቱ ለመልሶ ግንባታና ለግለሰቦችም ካሳ ማስፈጸም ሲገባዉ ዝምታን መርጧል።

    የክልሉም ሆነ የፌድራል መንግስት እንደ ተጠያቂነት ብሎም እንደ ባለቤትነት ትኩረት ሰጥተዉ አለማስፈጸማቸዉን   የተገነዘበዉ መጅሊስና አስተዋዩ ሙስሊም ማህበረሰብ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ፈጥኖ  መርሀ ግብር በመንደፍ በሀገር ዉስጥ እና ከሀገር ዉጭ ለሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰብ  መጅሊስ ጥሪ አቅርቧል።

    ይህንኑ የመጅሊስ ጥሪ ተከትሎ በዲያስፖራ የሚኖሩ ወንድምና እህቶች በአንድ ድምጽ የወገኖቻችንን እምባ እናብሳለን፤ እኛም ከጎናቸዉ ነን ፤ የነሱ ችግር የኛዉ ችግር ነዉ በሚል መርህ  ባደረጉት ርብርቦሽ በተለያየ መልኩ የተሰበሰቡ ገንዘቦች እንዲሁም ንብረቶችን ጨምሮ በገንዘብ ሲተመኑ እጅግ በጣም ከሚጠበቀዉ በላይ ሲሆን ታሪክም ሰርቶ አልፏል።

     በሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ በበድር ስር ካሉት ዉስጥ ለጊዜዉ በደረሰን መረጃ መሰረት ከተወሰኑት ኮምዩኒቲዎች ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር $20,000,000 (ከሀያ ሚሊየን ብር) በላይ ለመሰብሰብ መቻሉ እና ከሲያትል በተወሰኑ ወንድምች አንድ ሺህ ቁርአኖችን ከሀገር ዉስጥ ገዝቶ ለማቅረብ የተነየተ መሆኑና ይህ በእንዲህ እያለ ከበድር ዉጭ ያሉ ኮምዩኒቲዎችም መጠነ ሰፊ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ማከናወናቸዉ ይታወቃልና ከዚሁ አንጻር በዲያስፖራ የሚገኘዉ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳትፎ ምን ያህል የጎላ እንደነበር ማሳያ ሲሆን በሌላ መልኩ በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደምንችልም አሳዉቆናል።

    በዚህ መልካም ስራ በገንዘባችሁ ፤ በእዉቀታችሁ ፤ በጉልበታችሁ ፤ በንብረታችሁ ፤ በዱዐ (ጸሎት) ለተሳተፋችሁ ሁሉ አላህ (ሱወ) በአዱንያም በአኼራም አጅሩን ያብዛላችሁ እያልን ለዉጤቱም እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።  

አላሁ አክበር

በድር ኢትዮጵያ   ሰሜን በአሜሪካ   ማርች 3 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published