ሀገራዊ ጥሪ ከመጅሊስ

 

    በአማራ ክልል በሞጣ ከተማ በአሸባሪዎች ድርጊት ለተቃጠሉ መስጂዶች እና ለወደሙ የሙስሊሙ ንብረቶች የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ለማድረግ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አማካኝነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚተገበር መርሀ ግብር ተነድፎ ሥራዎች በፍጥነት መጀመራቸዉ ይታወቃል።

    ይህንኑ ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በዉጭዉ ዓለም ለሚኖሩ ወገኖችም በጋራ ጥሪ የቀረበ ስለሆነ በድር ኢትዮጵያም ይህንኑ ጥሪ ተቀብሎ እንደ ተለመደዉ ሁሉ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የሚጠበቅብን ወሳኝ ወቅት ላይ ያለን መሆኑን በመገንዘብ መልዕክቱንም ለሁሉም አካላት በግልጽ እንዲደርስ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ለበድር እህት ኮምዩኒቲዎች ፤ ለሌሎች ኮምዩኒቲዎች አና ለሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ እያስተላለፍን በዚህ ፈታኝ ወቅት ከወገን በላይ ደራሽ የለምና በሚቻላችሁ አቅም በየኮምዩኒቲያችሁ ፤ በቡድንም በግል በመሆን በመጅሊሱ የተጠየቀዉን መሰረታዊ ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዉን ለመመለስ መዘጋጀት ይጠበቅብናል ።

   የዉድመቱ መጠን በቀላል የሚለካ ጉዳይ ባለመሆኑ የችግሩን ስፋት ከግምት በማስገባት ቀደም ሲል ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ በተሻለ መልኩ መንቀሳቀስና የእርዳታ ጥሪዉንም ዉጤታማ እንዲሆን ጠንክራችሁ እንድትሰሩበት በአክብሮት ለማስታወስ እየወደድን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትም ለሞጣ ድጋፍ ማሰባሰቢያ በከፈተዉ የሂሳብ ቁጥሮች አማካይነትም ገቢዎች ወደ አንድ ማዕከል ፈሰስ እንዲደረጉ በማለት የተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮችንም አስታዉቋል።

  1. 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  1000315148457      ቀራንዮ ቅርንጫፍ  
  2. 2. ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ   1000054280428       አባነፍሶ ቅርንጫፍ   
  3. 3. አዋሽ ባንክ  01304069690301       ልደታ ቅርንጫፍ                                                                               

            በድር ኢትዮጵያ    ሰሜን አሜሪካ       ጃንዋሪ 27 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published