ሀጅ መሀመድ ሰኢድ ወደ አኼራ ሄዱ

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁኡን  

 ሀጅ መሀመድ ሰኢድ ወደ አኼራ ሄዱ

ነዋሪነታቸዉ በቶሮንቶ ካናዳ የነበሩት ሀጅ መሀመድ ሰኢድ በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ከትላንት በስቲያ አፕሪል 29 2020 ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ታዉቋል።

  ሀጅ መሀመድ ሰኢድ በኢትዮጵያ የፓርላማ አባል በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በ1966 ቱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ንቅናቄም አወንታዊ አስተዋጽኦ ካደረጉ ጠንካራ አባላትም ዉስጥ አንዱ መሆናቸዉና ለመጀሊስ መቋቋምና ዉጤታማነት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ካደረጉት አስተዋጽኦዎች መካከል ጥቂቱ እንደሆነም ይነገርላቸዋል።

   ወደ ቶሮንቶ ካናዳ ከመጡም በኋላ በሀገራችን የሙስሊሙን ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ድምጽ ከፍ አድርገዉ በማሰማት ሌት ተቀን ሰለቸኝ ሳይሉ እንዲሁም የቶሮንቶ በረዶ ሳይበግራቸዉ ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ታግለዉ ያታገሉ ነበሩ።

   ሰዉ ሁሉ ሞትን ይቀምሳታል ነዉና እሳቸዉም በዚህ በተከበረዉ የረመዳን ወር ወደ አኺራ ሄደዋልና አላህ (ሱወ) ጄነትን እንዲወፍቃቸዉ በድር ኢትዮጵያ እየተማጸን ለመላዉ ቤተሰባቸው እና ለቶሮንቶ ኮምዩኒቲም መጽናናትን እንመኛለን።   

አላሁ አክበር

   በድር ኢትዮጵያ   ሰሜን አሜሪካ     ሜይ 1 2020                                       

 

 

Leave a comment

All comments are moderated before being published