(በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ)        

        የአላህ ሰላምና እዝነት በነቢዩ  ሙሀመድ (ሰወ) እና በቤተሰቦቻቸዉ እንዲሁም  የእሳቸዉን  ፈለግ በተከተሉት ላይ ይሁን

               ታስረዉ ከተፈቱ ወንድሞቻችን የቀረበ ጥሪ                                            

  "There is no good in many of their conferences except the conferences of such as enjoin charity, or goodness, or the making of peace among men. And who so does that, seeking the pleasure of Allah, We shall soon bestow on him a great reward." (Surah Nisaa: 114)

      በድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ባሳለፋቸዉ አስራ አምስት ዓመታት በሀገራችን በእምነት ነጻነት ላይ በሚከሰቱብን ችግሮች ልዩ ትኩረት በመስጠት መሰረታዊ የሆነ አወንታዊ ለዉጥ ለማምጣት ከህዝቦች እና ከመንግስት ጋር በተለያየ ጊዜ በደብዳቤ ልዉዉጥ እንዲሁም በአካል በመገኘት ጥረቶችና ሙከራዎች አድርጓል።  

      የህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ ፤ ህገ መንግስታዊ የመብት እና የእምነት ጥያቄ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ከተከሰተበት ወቅት ጀምሮ ለሰላማዊ ትግሉ አስፈላጊዉን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ እንዲሁም ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ለቀረቡ መሰረታዊ የእምነት ጥያቄዎች ተገቢዉን ምላሽ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸዉ መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመነጋገር መፍትሄ ለመሻት የበኩሉን ጥረት አድርጓል።  የመፍትሄ  አፈላላጊ ኮሚቴዎችም ከታሰሩ በኋላ ጥረቱን የቀጠለ ሲሆን በተለይም የታሳሪ ቤተሰቦችን በመደገፍም ሆነ ከፍርድ ሂደቱ ጋር ተያያዥነት ባላቸዉ ጉዳዮች የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል።

      የሙስሊሙ ማህበረሰብ ያቀረባቸዉ መሰረታዊ ሶስቱ የእምነት ጥያቄዎችና ከመፍትሄ  አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን መታሰር ጋር በተፈጠሩ ችግሮች ከመንግስት ጋር ለመወያየት በ፪ሺህ  የበድር ልዑካን ቡድን መላኩ ይታወቃል። ምንም እንኳ በተላያዩ መሰናክሎች የልዑካን ቡድኑ ተግባር በወቅቱ ለመቋጨት ባይቻልም በጥሩ ጅማሮ በእንጥልጥል መመለሱ ይታወቃል።  ሆኖም በበድር አማካይነት ቀደም ሲል ተጀምሮ የነበረዉ የሽምግልና ሂደት እንዲቀጠልበት ታስረዉ ከተፈቱ ወንድሞቻችን ጥያቄ ለበድር መቅረቡን ከየ ኮምዩኒቲ አመራሮች ጋር በጋራ ባደረግነዉ ዉይይት ወቅት መግለጻችን ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የቀረበዉን ጥሪ ተቀብሎ በአላህ (ሱወ) ፈቃድ ዉጤት ላይ ለማድረስ በቅርቡ የበድር የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ መሆኑን አዉቃችሁ ጥረታችን ይሳካ ዘንድም በዘወትር ዱዓችሁ ታስታዉሱን ዘንድ በማክበር ለመግለጽ እንወዳለን ።

 

    አላሁ አክበር                   

                                                                                                       በድር ኢትዮጵያ አለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት

     የዳይሬክተሮች ቦርድ

     ሰሜን አሜሪካ

     FEBRUARY 2016

16th Annual Badr Convention in Nashville (click to see article in English) 

(በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ)

      የአላህ ሰላምና እዝነት በነቢዩ  ሙሀመድ (ሰወ) እና በቤተሰቦቻቸዉ እንዲሁም  የእሳቸዉን  ፈለግ በተከተሉት ላይ ይሁን

"There is no good in many of their conferences except the conferences of such as enjoin charity, or goodness, or the making of peace among men. And who so does that, seeking the pleasure of Allah, We shall soon bestow on him a great reward." (Surah Nisaa: 114)

16ኛዉ የበድር ጉባኤ  በናሽቭል

     በድር ኢትዮጵያ ከተቋቋመ እነሆ አስራ ስድስተኛዉን አመት አስቆጥሯል፤ በእነዚህ አመታት ዉስጥ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናዉን መቆየቱ ይታወቃል፤ከሚያከናዉናቸዉም ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንደኛዉ በየአመቱ በሚካሄደዉ በበድር ኢትዮጵያ አመታዊ ጉባኤ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በማገናኘት የዳዋ  ፕሮግራሞችን ከመተግበሩ አልፎ በተለያዩ አበይት ርእሶችና በወቅታዊ ችግሮች ላይ በመወያየት የመፍትሄ  ሀሳቦች መሻትን ያካትታል።

     በዘንድሮም ዓመት አስራስድስተኛዉን የበድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዘጋጅነት  በተመረጠዉ  በናሽቭል ተኒሲ እንደሚካሄድ ስናበስር ከታላቅ ደስታ ጋር ነዉ!!   

      በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከሰሜን አሜሪካ ግዛቶች እንዲሁም ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎችን ጨምሮ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች አንድነታቸዉን ለመግለጽና እስላማዊ ወንድማማችነታቸዉን ለማጠናከር ብሎም በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ለመመካከር ወደዚሁ ይተማሉ። ከ (ሀምሌ) JULY 28 እስከ 31 /2016 በሚካሄደዉ በዚሁ ታላቅ ጉባኤ ተካፈይ ይሆኑ ዘንድ በድር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት በታላቅ አክብሮት ጥሪውን ያቀርባል።

አላሁ አክበር !!!

በድር ኢትዮጵያ አለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ሰሜን አሜሪካ

DECEMBER  2015