ኢ ድ   ሙ ባ ረ ክ

ኢ ድ    ሙ ባ ረ ክ  

      በሰሜን አሜሪካ ፤ ካናዳ ፤ በሀገራችን ኢትዮጵያ ብሎም በዓለም ለምትገኙ ሙስሊሞች በሙሉ እንኳን ለ1441ኛዉ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል አላህ (ሱብሁዋነሁ ወተአላ) በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።  

    ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለችበት አሳዛኝ ሁኔታ በተለይ ንጹሀን ዜጎች በግፍ የተገደሉበትን ሂደት ያሳለፍንበት መሪር ጊዜ መሆኑ ለሁሉም ማህበረሰብ ግልጽ ነዉ። ይህንንም ክፉ ጊዜ ተሻግረን ህዝቦች በሰላም በፍቅር እና በመተሳሰብ ሊኖሩባት የሚችለዉን የጋራ ሀገር መገንባት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባልም እንላለን ።   

     በዓለም የተከሰተዉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝም ሀገራችንን እየተፈታተነ ይገኛል፤በሽታዉን በተቻለ መጠን    ለመከላከል እንዲቻል ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክሮች ተግባራዊ በማድረረግ ከመቼዉም በተሻለ መልኩ ህዝቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ዘወትር ሊያደርግ እንደሚገባ ለማስታወስ እየወደድን በዚሁ ተላላፊ በሽታ ሳቢያ የዘንድሮ የሀጅ ስነ-ስርዐትም ተስተጓጉሎዋል ፤ መሳጂዶቻችንም ለረጅም ጊዜ ተዘግተዋልና ፈጣሪያችን  አላህ በቸሩ በቃችሁ ብሎን ያስወግድልን ዘንድ እንደሁሌዉም እንማጸነዋለን።     

      በዓሉ የሰላም የፍቅርና የነጻነት ተምሳሌት እንዲሆንልን በመመኘት በሀገራችን በተከሰተዉ ብጥብጥ ሳቢያ ቤት ንብረታቸዉ ለወደመባቸዉና ከቀዬአቸዉ ለተፈናቀሉ ወገኖች ሁሉ ልዩ ትኩረት በመስጠት በማስታወስና በመርዳት በዓሉን በጋራ ልናሳልፍ ይገባል እያለ በሀገራችን ፍትህና እኩልነት እንዲሰፍን ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ጥረት እንዲያግዝ እያሳሰብን በድር ኢትዮጵያ መልካም የበዓል ምኞቱን ይገልጻል።

  አላሁ አክበር

በድር ኢትዮጵያ   ሰሜን አሜሪካ     ጁላይ 30, 2020                          

Leave a comment

All comments are moderated before being published