ኢድ ሙባረክ

ኢ ድ   ሙ ባ ረ ክ

    ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁም በዓለም ለሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለ1441 ኛዉ የኢድ አል ፊጥር (የረመዳን ጾም) በዓል አላህ (ሱ.ወ) በሰላም አደረሰን በማለት በድር ኢትዮጵያ ታላቅ ልባዊ ደስታዉን ይገልጻል።

   በዓለማችን የተከሰተዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከመስጂድ እንዲርቅ ቢያስገድደዉም ባለበት ሁሉ ዱዐ (ጸሎት) በማድረግ ፈጣሪዉን ሲማጸን መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በቀጣይ ከዓለማችን በሽታዉ እስኪወገድ ጸሎቱን በበለጠ ልንቀጥልበት የሚገባ አቢይ ጉዳይ ነዉ። አላህ (ሱ.ወ) በሽታዉን ያስወግድልን ዘንድም እንማጸነዋለን።

    የዘንድሮዉ በዓል ልዩ የሚያደርገዉ ለሀገራችን እና ለአፍሪካ ኩራት ብሎም ተምሳሌት በሆነዉ በንጉስ ነጃሺ (ፍትሀዊ መሪ) የተሰየመዉ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል በሀገሪቱ ርዕሰ ከተማ ለመገንባት የሚያችል 30000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለዉ ቦታ ላይ ርክክብ ተፈጽሞ የመሰረት ድንጋይ መጣሉ ነዉ። ለዚሁም የተቀደሰ ተግባር ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነዉ። በቀጣይም በጉጉት የሚጠበቀዉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ህጋዊ ሰዉነት ኖሮት በአዋጅ  ለማቋቋም የሚደረገዉ ሂደትም በቅርቡ ጸድቆ ለዉጤት እንደሚበቃ በመተማመን ነዉ።

    በዓሉም የሰላም ዘመንን እንዲያስከትልልን በመመኘት የሁሉም ሙስሊም ሀላፊነት የሚሆነዉ በተለይ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተገናኘ ለተጎዱ ወገኖቻችን ልዩ ትኩረት በመስጠት እንድናስታዉሳቸዉ ሆኖ አቅመ ደካሞችን በመዘየርና ለበዓል መዋያ የሌላቸዉን ደግሞ በመርዳት በዓሉን በጋራ እናክብር እያልን ዳግም እንኳን ለበዓሉ አደረሳችሁ እንላለን።

አላሁ አክበር

 በድር ኢትዮጵያ   ሰሜን አሜሪካ  ሜይ 22 2020

Leave a comment

All comments are moderated before being published